Friday, November 13, 2015

ኃ/ማርያም ደሳለኝ በቅርብ ያሉት 250 ሚሊዮን ኩንታል እህል ዬት ገባ? አሁን ለተራቡት 15 ሚሊ. ህዝብ ፈረንጆቹ እጃቸዉን ልዘረጉ ነዉ፤ ከዚህ በፊት በደርግ ጊዜ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመጣ 95 ሚሊ. ዶላር እንዳለ ወያኔ እጅ እንደገባ፣ አሁንም ምን ዋስትና አለ?

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከጥቂት ጊዜ በፍት  አትዮጵያ በምግብ ራሷን መቻሏን እንድህ ብሎ ተናግሮ ነበረ፣  “በሁለት አስርተ ዓመተ ዉስጥ ሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ኩንታል በማምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በምግብ ራሳችን ችለናል…” ብዙም ሳይቆይ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ለመደበቅ ብሞክርም ነገሩ የሰዉ ነብስም ንለሆነ የምግብ እጥረትና የረሀብ ነገር በኢትዮጵያ መኖሩ የዓለም አቀፍ አጀንደ እየሆነ መጥተዋል፡፡ ፈረጆቹም ከዚህ በፊት የዉሽማቸዉ የወያኔ መንግስት የሚለዉን እንድገት ባወደሱበት አፋቸዉ አሁን ግን  የኢትዮጵያን ረሃብ እየተቀባበሉ ዘግበዋል፡፡ኢትዮጵያ ከአፍረካ ሀገራት ሁሉ በፍትነት እያደገች ናት እየተባለች ድሮ የሚትታወቅበት የረሃብ ማለያ ለብሳ ብቅ አለች፡፡  ዛሬ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን መራብ ማለት ትልቅ ዉርደትና ዉድቀት ነዉ፡፡ 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለሌላ ሀገር ትልቅ ትረጉም አለዉ፡፡ ለምሳሌ የስውድን ሀገር አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት ሲናይ 9 ሚሊዮን ሲሆን፣ የኖርዌይ ደግሞ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ነዉ ያላቸዉ፡፡ 15 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማራብ ማለት የኖርዌይና የስውድን ህዝብ በሙሉ እንደተራቡ ናቸዉ ማለት ነዉ፡፡

ከዛሬ ጥቂት ወራት በፊት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ እንዳሉት ኢትዮጵያ ብዙ እህል እያመረተች በምግም ራሱዋን ችላለች ብሏል፡፡ ወገኖቻችን ሲራቡ ምግቡ ዬት ገባ? ብዙ የዉጭ ሀገር እንቨስተሮችም በእርሻ መሰማራቸዉን እናዉቃለን፡፡ መሃመድ ሁሴን ዓሊ አልሙድ ራሱ ሰፊ የእርሻ መሬት ወስዶ ሌላ ነገር ይቅርና በኢትዮጵያ የማትታወቀዉ ሩዝ ራሱ ማምረት ጀሚሮ ነበረ፡፡ እሱ ብቻ አይደለም ብዙ የትግራይ ተወላጆች በእንቨስትመንት ስም በተለያየ ክልሎች፣ በተለይ በጋንቤላና በቤንሻንጉል ጉሙዝ በእርሻ ስራ እንደተሰማሩ የአደባባይ ምስጥር ነዉ፡፡ እና ምግቡ ዬት ገባ


ቻናል 4.ኮም የተባለ የዉጪ ሚድያ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ መሬት ወረራና የዉጪ ሀገር ባለሀብቶች በእንቨስትመንት ስም ብዙ መሬቶች ከገበሬዎች ተቀምተዉ ተሰጥተዋቸዉ በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተዉ እንዳሉና የተመረተዉ እህል ራሱ ወደ ዉጪ ሀገር እንደሚላክና ነገሩ ረሃብን እንደሚያስከትል ዘግቦ ነበረ፡፡ ጆሮ የሰጠዉ ሰዉ የለም እንጂ የመሬት ወረራና የተመረተ እህል ወደ ዉጪ የመላክ ጉዳይ አደጋን እንደሚያስከትል የዉጪ ሚዲያወች በግልጽ ዘግቧል፡፡ እዚህ በዉጭ ሀገር ከሀሻዎች ሆቴልና ሬሰቶራንት የጤፍ እንጄራ በብዛትና በቅንጦት በብዙ ብር ሲበላ የጤፍ አምራቹ ግን እየተራበ ናቸዉ፡፡ በጎሮቤት  ሀገር ኤርትራም ጤፍ ባይመረትም የኤርትራ ሕዝብ ዛሬም የጤፍ እንጄራ እየበላ ነዉ፡፡ 


በደርግ ጊዜ በብዙ ኢትዮጵያ ቦታዎች  በተከሰተ ረሃብ ምክስያት ብዙ ሰዎች ሞተዋል፡፡ ፈርንጆቹም ለኢትዮጵያዉያን ለመድረስ ሲሉ  ብዙ ሚሊዮን ዶላር ሲላግሱ፣ ፈረንጆቹ ለኢትዮጵያ ህዝብ የለገሱት ወደ 95 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ግን እንዳለ ወያኔ እጅ በመግባት ለመሳሪያ ግዢና ለጥቅማቸዉ መዋሉን ቢቢሲ የቀድሞ የወያኔ ባለስልጣናት፣ አሁን ግን ከወያኔዎቹ ጋር ሳይስማሙ ቀርተዉ በዉጪ ሀገር በስደት የሚኖሩ  አረጋዊ በርሄና ገ/መድህን አራያ  የተባሉት ሰዎችን  ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል፡፡ http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/8535189.stm   


የወያኔዎቹ የደደቢት ቁጠባ ማህበር ያለዉ ብር፣ የኢትዮጵያ በሔራዊ ባንክ ራሱ የለዉም… ተብሎ በስፋት በኢትዮጵያ ዉስጥ ሲወራ በጋዘጠኛ ጆሮ ሰምቸ ነበረ፡፡ እንደሁም ይሄንን ሁሉ ብር ከዬት ነዉ ያገኛችሁት ተብሎ ሲጠየቁ፣ ወያኔዎቹ ከበረሃ ነዉ ያመጣነዉ ብለዉ መልስ መስጠታቸዉን ህዝቡ ሲናገር ሰምቻለሁኝ፡፡ አቶ ገ/መድህንና አረጋዊ ያረጋገጡም  ገምሱ ይሄንኑ ይመስለኛል፡፡  ዛሮም ብሆን የምዕራብያዉያንና የቻይና መንግስት የተራቡ ኢትዮጵያዉያን ለመርዳት እየተረባረቡ ናቸዉ፡፡ የኔ ጥርጣረ ግን እንደ በፊቱ ወያኔወቹ ከዉጪ የሚመጠዉን እርዳታ  ለራሳቸዉ ጥቅም ብያዉለዉስ የሚል ስጋት አድሮብኛል፡፡  
 ሌላ  የገረመኝ ነገር ኢትዮጵያዉያን በረሃብ እያለቁ ባሉበት ባሁኑ ጊዜ የወያኔ መንግስት የጦር ታንኮችን እያመረተ ለአፍርካ ሕብረት እየሸጠ ነዉ የሚል ዘገባ ትግራይ ኦንላይን የሚባል ድህረ-ገጽ የሲሲቲቭ ሪፖርት አያይዞ ፅፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ የወያኔ የግል ንብረትና የወያነዎቹ ዋነኛዉ ብዝነስ መሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ጠንቅቆ ያዉቃል፡፡ http://www.tigraionline.com/articles/ethiopia-makes-tanks.html


 እንደ አንድ ሰዉ እኔ የሚለዉ፣ ማንኛችንም ከዛቺ ከኢትዮጵያ እምፓየር ዉስጥ የመጣንና በዉጪ ሀገር በስደት የሚንኖር ወገኖች ሁሉ ባገር ቤት ለተራቡት ወገኖቻን ድምጽ በመሆን ባንድነት መቆምና መጮህ አለብን፡፡ በተበታተንን ቁጥር ወያኔ በታተኖን ይጨርሰናል፡፡ወያኔ በጥይትና በእራት እየጨረሰ ያለ ማንን ነዉ?  አሁን የተራቡት 15 ሚሊዮን ህዝብ እነ ማን ናቸዉ? ከትግራይ ክልል የራያ ህዝብ ከሌሎች ትግራይ ህዝብ ተለይቶ ለምን ተራበ…?  


  

Tuesday, November 10, 2015

Woyyaanneen qorsa woggaa isii dheereffattu dabaan qotataa jiraatti malee silaa amma hin geettu. Cidhuu qorsa woyyaanee keessa faranjoonnille hin dhabamanu! ወያኔ እድሜ ማራዘሚያዉ የተንኮል ክኒን እየቀመሜ ነዉ እንጂ እዚህ አትደርስም ነበረ! ከቅመማዉ በስተጀርባ ፈረንጆቹም አይጠፉም!


Woyyaanneen qorsa  woggaa isii dheereffattu dabaan qotataa jiraatti malee silaa amma hin geettu. Cidhuu qorsa woyyaanee keessa faranjoonnille hin dhabamanu! Woyyaaneen muddama keessa yoo seentu ajandaa dabaa giduu keennatti uumti. Yeroo nuuti wocnu, isiin goomittaafi bayyanata argattee, dandamattee ka’uun mala biraa ittiin nu dhabamsiitu malattee as baati. Hedduun keenna garuu shira Woyyaane’ee kana bareechinee hin beeknu. Dhiheenna kana raadiyoon BBN jedhamu odeeffannoo tamsaaseen akka jedhetti, “viidiyoon pirootestaantonni of ijaaruun magiida keessa seenanii dhoksaadhaan hojii hojjata jiran harkaa saaxilameera” jechuun gabaaseera. Ani Viidiyoo sanille ilaalee gaaffiifi yaada natti dhaga’ame barreeffama gabaabaa armaan gadiitiin ibsuuf yaaleera:
  1. Namichi ‘paasterii’ jedhamu kan viidiyoo warabuu sun, tajaajilaa waldaa kiristaana kamiiti? Namni maqaa isaa beeku  jiraa?
  2. Namichi ‘paasterii’ jedhame kun, afaan Amaaraa inni haasawu, Amaariffa Tigiroonni haasa’an fakkaata.
  3. Namichi ‘paasterii’ jedhamu sun nama fakkeessu yookiin haasawa kaabinee fakkaata malee, paasterii natti hin fakkaanne.
  4. Viidiyoo san yoo ilaaltane baay’ee kukkutameera; yeroo hedduullee  idiitii ta’eera, yookiin gulaalameera.
  5. Vidiyoon sun hujii forfoqaandaa ykn  propogaandaa siyaasaatiif waan hojjatame malee, waan ragaa amantaa bahuuf waraabame hin fakkaatu.
  6. Jecha namchi uffata Musiliimaa uffatee jedhe, “Masgiida hundeessaan dhaaba Adda Bilisa Baasaa Islaama Oromiyaa, Jaarraa Abbaa Gadaa maatii isaatiif ijaare keessalle seenneerra…” jechuun haasawe kun, ergaa siyaasaa oofate moo, erga amantaattu caalaa dubbatamee…?
Gabaabumatti ani akka nama tokkootti wonni jedhu, Woyyaaneen aangoo isiirraa turuuf cubbuu isiin hin hojjanneefi qorsi isiin hin qonne hin jiru. Seena’anille ta’ee qabatamaan, biyya impaayeera Itoophiyaa jedhamtu san keessatti, saboonni adda addaatiifi uummanni amantaalee garaa garaa qaban wal-kabajuun jiraataa, addunyaafille fakkeenna guddaa ta’aneeran jedhama. Woyyaaneen hardha kufuuf yoo tittimtu yookiin gitintirtuufi, akkasuma du’uuf yoo dhidhiitattu, amantaafi saboonni isiin itti hin buuneefi hin dhiitiin hin jiru. Amantaa Ortodoksii naannoo Tigiraayii irraa kan hafe malee, kan naannoo Amaaraatiin wal-dhabdeerti Woyyaaneen. Impaayeera Itoophiyaa san keessatti, akkuma baay’ina uummataan dursa qabatee jiru, hordoftoonni amantaa Islaamaatiifi Pirostestaantiille Oromoo akka ta’an wal-nama hin gaafachiisu.
Diddaafi qabsoo mootummaa Woyyaanee kanarratti finiintee jirtu kallattii jijjiiree qumaarii umurii isii dheereessu taphachuuf,  Musiliimotaafi hodorftoota amantaa Pirootestaantii wolitti buusuuf fiishikaan waan afuufame fakkaata. Woyyaaneen woggaa bitiinsa gita bittaa isii dheerefachuuf yeroo waamicha walitti bu’iinsaa nuuf dhiheessitu, dabaafi cubbuu isii kanatti dammaqnee, amantaaleefi yaadawwaan garaa garummaa jidduu keennaa qabnu waliif kabajnee, tokkummaan kaanee shororkeessaa mootummaa Woyyaaneetiifi ‘qanbara’ (wanjoo) Woyyaane’ee ofirraa darbachuu qabna. Shororkeessaa kan ta’e mootummaan Woyyaanee hanga hin dhabamsiifaminitti, nuutille taane moo, amantaan keennalle nageya hin argatu!   



ወያኔ ትንቅንቅ ዉስጥ ሲገባ ለእኛ አጀንዳ ይፈትራል፡፡ እኛ ሲንጫንጫ እርሱ እፎይታን ያገኝና አገግመዉ አኛን ለማጥፋት በሌላ ዘዴ ብቅ ይላል፡፡ ብዙዎቻችን ግን  የወያኔን ተንኮል በደንብ አናዉቅም! በቅርቡ BBN ሬድዮ ባስተላለፈዉ መረጃ መሰረት “በመስግድ ወስጥ የተደራጁ ፕሮስታንቶችን የሚያጋልጥ በምስጥር የተቀዱ ቪድዮ ተጋልጠዋል…”፡፡ ቪድዮዉንም ተመልክቸ የተሰማኝ ጥያቄና ሃሳብ እንድሚከተለዉ በአጭር ፅሑፍ ምልክ አንስቻለሁኝ፡                       


  1. ቪድዮ ቀጂ ፓስተሩ የዬት ቤተክርስቲያ አገልጋይ ነዉ? ስሙን የሚያቅ ሰዉ አለ? ከዚህ በፊት በፓስተርነት የሚያዉቀዉ ሰዉ አለ?
  2. ፓስተሩ ነዉ የተባለ ሰዉየዉ የሚያወራ አማሪኛ ትግሬዎቹ የሚያወሩ አማርኛ ነዉ የሚመስለዉ::
  3. ቪድዮ ለምን መቅዳት አስፈለጌ? ከስፈለጌ እንደዛ አይነት አደራሽ ለምን አስፈለገ? አደራሹ የሰኩሪቶች ቦታ ነዉ የሚመስለዉ::   
  4. ፓስተር የተባለ ራሱ የሚያስመስል ሰዉ ወይም ካቢኔ ይመስላል እንጂ እርሱ የሚለዉ የፓስተር ቃል አይመስልም፡፡  
  5. ቪድዮ በጣም ተቆራርጠዋል፣ ብዙ ጊዜ ኤድት ተደረገዋል፤ ለምስክርነት የተቀዳ አይመስልም፡፡
  6. ቪድዮ ለወንጌል ስብከት ሳይሆን ለፓለትካ ስራ የተሰራ ይመስላል፡፡
  7. “የኦሮሚያ እላምክ ፍሮንት መስራች ጃራ አባ ገዳ ለቤተሰባቸዉ የሰራ መስግድ ዉስጥም ብተናል…” ብሏል ሪፖርት አቅራብዉ፤ ይህ አሁን ሃይማኖታዊ መልክቱ ነዉ ወይስ የፖለቲካ መልእክቱ ይበልጣል…?


ባጭሩ እንደ አንድ ዜጋ እኔ የሚለዉ፣ ወያኔ ስልጣንን ለማራዘም የማይቀምም መድኃንት፣ የማይቆፍር ጉድጓድና የማይነቅል ድንጋይ የለም፡፡ በታሪክም ሆነ በተግባር፣ ኢትዮጵያ ተብላ በሚትጠራ ሀገር ዉስጥ በዙ ብሄሮችና የተለያዩ ሃይማኖቶች በሰላም ተቻችሎ በመኖር ለዓለም ምሳሌ ሆነዋል፡፡ወያኔ ለመውደቅ ሲንገደገድ ያልተላተመበትና ያልረገጠ ብሄሮችና ሃይማኖቶች የሉም፡፡ ከትግራይ አከባቢ ኦርቶዶክስ በስተቀር ወያኔ ከአማራ አከባቢ ኦርቶዶክስ ጋራ ተጣልተዋል፡፡ከዋቄፋታና ከሙስሊሙ ህብረተሰባችን ጋር ተጋጭቷል፡፡ በኢትዮጵያ እምፓዬር ውስጥ ልክ እንደ ብሔሩ ብዛት የሙሲልምም ሆነ የፕሮተስታንት ተከታዮች በብዛት ኦሮሞ መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ አሁን በከፍተኛ ደረጃ ጎልተዉ እየታየ ያለ የህዝብ ተቀዉሞና ትግል ለመቀልበስ ሙስሊሞችንንና ፕሮስታቶችን አጋጭተዉ የፖለቲካ ቁማር ለመቆመር ፊሽካዉ የተነፋ ይመስላል፡፡ ወያኔ የራሱን እድሜ ለማራዘም እኛን የሚያጋጭ ጥር ሲያቀርብልን፣ በወያኔ ተንኮል ነቄ ብለን የእርበርሳችን ሃይማኖቶችን በማክበር፣ በአንድነት ተነስተን በጥባጭ የወያኔን ሥርዓት ማስወገድ አለብን፡፡ በጥባጭ የወያኔ መንግስት ካልተወገደ አኛም ሆኔ ሃይኖታችን ሰላም አናገኝም!        



የኦሮሞ ሕዝብ ፀረ-ልማት አይደለም፤እንደዉም የኢትዮጵያ የልማት አባት ነዉ እንጂ!


እንደሚታወቀዉ ከአጼ ምኒሊክ በፊት የዛረዉቱ ኢትዮጵያ የዛሬ ቅርጽ አልነበራትም፡፡ በኦሮሚያም ሆነ  በሌሎች ክልሎች ዉስጥ የሚገኙት ከተሞች አመሠራረታቸዉ ለነፍጠኞች ሠራዊቶች ሲባል  ከአዉሮፓ  ባገኙት ነፍጥ (በዘመናዊ የጦር መሣሪያ) የአከባብን ሁኔታ ከቁጥጥራቸዉ ስር  አስገብተዉ  ከሠፈሩበት በኋላ ነገሩ ከተመ ወይም ከተማ አሉት፡፡አጼ ምኒሊክ ለአዉሮፓዉያንና ለአሜርካዉያን የኢትዮጵያን ልጆች ለባሪያ ንግድ በመሸጥ በለወጡት በጦር መሳሪያ ኦሮሞዎችን፣ ደቡቦችን፣አፋሮችን፣ሱማሌዎችንና ወዘተ በጦር መሳሪያ እየለወጡ፣ እንዲሁም ባገኙ በጦር መሳሪያ፣ የተለያዩ  የበፊቱ የኢትዮጵያን ግዛቶች እንደ ኦሮሞ፣አፋር፣ከፋ፣ዎላይታ፣ወዘተን በመስበር የዛሬይቱ ኢትዮጵያን ፈጠሩት፡፡  
 
የነፍጠኞች ወታደሮች የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችን ለማስገበር ሲሉ ወደ ተለያዬ የኢትዮጵያ ክፍሌ አገሮች ዉስጥ ሲሰራጩ፣ የወታደሮች ካምፕ ይመሰርቱ ነበረ፡፡ ነፍጠኞቹ ግዛታቸዉን ሲያከትሙ ነዉ ከተማን የመሰረቱት፡፡ በኦሮሚም ሆነ በሎሎች ክልሎች ዉስጥ ከተማ ሲከተም በሃይል፣ በግዳጅ፣ በግድያ፣በቅሚያና በወዘተ ነዉ ከተማ የተከተመ፡፡ ነፍጠኞቹ ወደ ተለያዬ የኢትዮጵያ ክፍሌ አገሮች ዉስጥ ሲሰራጩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይም የነበሩ፤በፊዉዳሊዚም ጊዜም ገበሬ ከሚያርሰዉ ምርት 1/3 ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚሰጥ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ አማርኛ ቋንቋ በብዛት በኢትዮጵያ ከተሞች ዉስጥ ለሚነገርበት ዋነኛዉ ምክንያትም ይህ ሆነዉ ነዉ እንጂ የቋንቋዎች ንጉስ ሆነዉ አይደለም፡፡ 
 
መታየት ያለበት ሌለ ጉዳይ ደግሞ በተለይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በጉሙዝና በወዘተ ዙሪያ  የሚገኙ ከተሞቸ ዉስት በብዛት የሚኖሩ የአከባብ ተወላጆች አይደሉም፡፡ ዛሬም ብሆን በእነኚ የክልል ከተሞች ዉስጥ በብዛት የሚነገረዉ ቋንቋም አማርኛ ነዉ፡፡ አማሪኛ ለምን ተነገሬ ማለቴ አይደለም፤ ቋንቋ ሀብት ነዉና፡፡ እኔም አማርኛ በመቻሌ ነዉ ሀሳቤን በአማሪኛ እየገለጽኩኝ ያለሁት፡፡ ዋና ቁምነ ገሩ ግን  ማንኛዉም ሰዉ ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራት፣መጉበኘትና ወዘተ ይችላል፡፡  ይህ ሰዉ ግን ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራትና መጉበኘት የሚችለዉ የአከባቢዉን ሕብረተሰብ ቋንቋንና ባህልን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ዛሬ ግን በሌሎችም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የሚናየዉ ነገር በጣም የሚገርም ነዉ፡፡ በአጼዎች ጊዜ አማርኛ እንደ የንጉስ ቋንቋ ተወስደዉ፣ ሌላዎቹን ግን የማንቋሸሽና የመናቅ አዝማሚያ ይታይ ነበረ፡፡ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋትም ሆነ በብሄር ብዛት ኦሮሚያና ኦሮሞ መሆኑን የሚክድ ሰዉ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሆነዉም ግን የኦሮሞ ህዝብ ከአጼዎች ዘመን ጀሚሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከስርዓቱም ሆነ ከከተማ ያገኘ ጥቅም የለም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ያገኘ ነገር ብነገር ከቦታ መፈናቀል፣ተመልሰዉ አገልጋያቸዉ መሆን፣የራሱን ቋንቋ ማጣት፣ሳይወድ በገዛ አገሩ የሌለ ብሄር ቋንቋና ባህል መቀበል (assimilation) ና የመሳሰሉት ግፎች ደርሶበታል፡፡ እዚህ ላይ የቀዲሞ የኢትዮጵያ የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩ  አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በዲሮና በአሁኑ ስርዓት በኦሮሞች ላይ  የተፈጸሙትና አሁንም እየተፈጸሙ ላሉት ግፎች የሚዘገንን ሲለመሆኑ ለኢሳት ቴሌቪዥን በ2014 በሰጠ  አስተያየት፣ ከወያኔ ጋር በሰራባቸዉ ጥቂት ዓመታት ዉስጥ ለሪልስቴቶች ብቻ  ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከ29 የገጠር ቀበሌዎች 150.000 (መቶ ሃምሳ ሺህ) ኦሮሞዎች  ተፈናቅለዉ የገቡበት አይታወቅም ብሏል፡፡ ኦሮሞቹን አፈናቅለዉ  እንደ ሀያት ሪልስቴቶች የሰሩት የወያኔ ቱባ ባለስልጣኖች መሆናቸዉን አቶ ኤርሚያስ በጠሰዉ ቃለ-ምልልስ ተናግሯል፡፡ 
 
ከተማንና ኦሮሞን በተመለከተ ሌላ ግፍ፣የሚገርም ነገር ብኖር፣ እኔ ራሴ በአይኔ ያየሁት ነገር፣ አንዳንድ በኦሮሚያ ከተሞች ዉስጥ የተወለዱት ልጆች ኦሮሚኛ አለመቻላቸዉ ሳይሆን የገረመኝ፣እናት አማርኛ አትችልም፤ ልጇ ደገሞ ኦሮሚኛ አትችልም፡፡ እንደዚህ አይነቱ የተዛባ ህብረተሰብ እስከ መቼ  ነዉ የሚንፈጥረዉ? ግን ለምንድ ነዉ በኦሮሞና በኦሮሚኛ ላይ የማጥፋት ዘመቻ የሚከፈተዉ?  በኦሮሚያ እንብርት በሸገር-ፊንፊኔ ከተማ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተንቀዉ የዉጪ ሀገር ቋንቋዎች እንደ ፈረሳይኛና አረብኛ በትምህርት መልክም ይሰጣል፣ በብዙሃን መገናኛም ይነገራል፡፡ ኦሮሞ ይሄንን አይቶ ልክ አይደለም ብለዉ ተቃዉሞ ሲያቀርብ ምኑነዉ ጥፋቱ፣ ምኑነዉ ጠባብነቱ? ወያኔም የራሱን ቋንቋ ከጉዳት ሲያድነዉ ኦሮሞኛን ኣባ ካና አላለም፡፡ ወያኔ ወደ ስልጣን ሲመጣ በመቀሌ ከተማ ራሱ ትግርኛ ጠፈቶ በአማሪኛ ተተክቶ እንደነበረና ከዚያ በኋላ ወያኔ በዱላ ማስመለሱንና ዛሬ ግን አማርኛ በትገራይ ክልልም ሆነ በመቀሌ ከተማ እንግዳ መሆኑን እኔ ራሴ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በሚማርበት ጊዜ ሰምቸም አይቼ ነበረ፡፡ 
 
ከላይ እንደ ጠቀስኩኝ ሁሉ፣ አሁንም ደገሜ እላለሁኝ፤ ማንኛዉም ሰዉ ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራት፣መጉበኘትና ወዘተ ይችላል፡፡  በሰላማዊና በሰነጠለ ዓዕምሮ ሲናይ ይህ ሰዉ ግን ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራትና መጉበኘት የሚችለዉ፣ የአከባቢዉን ሕብረተሰብ ቋንቋንና ባህልን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ በኦሮሚያ እያየን ያለነዉ ነግር ይሄን የሚቃረን ነዉ፡፡ እዉነት ብንናገር እኮ አሪፍ ነዉ! ሌሎች ብሄር በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች ክልሎች ሲኖሩ በነርሱ ቋንቋና ባህል ሊያስተዳደሩን አይችሉም፤እንድሁም ቋንቋችንና ባህላችንን ማጥፋትና መግደል የለባቸዉም፡፡ በባሕር ዳር፣ በጎንደርና በጎጀም በብዛት የሚኖረዉ ኦሮሞ ነዉ ወይስ አማራ ወይስ ትግሬ? በመቀሌ፣በአድዋና የመሳሰሉ ከተሞች ዉስጥ የኦሮሞ ህዝብ በነዋሪነት ይኖራልን? ወደ ኦሮሚያ ስንመጣስ፣ በሸገር፣በአዳማ፣በሻሻማኔ፣በአሰላ፣በድሬ ዳዋ፣ በነቀምት፣ በአዶላ፣ በጭሮ፣በያቤሎና በወዘተ የአማራ፣የትግሬ፣የደቡብ ብሄር ነዋሪ ብቆጠር እነርሱ ናቸዉ ወይስ ኦሮሞ ነዉ የሚበልጠዉ? አሁንም የሚገርማቹ ነገር፣ በብዙ የኦሮሚያ ከተሞች ዉስጥ የመዋለ-ሕጻናት ት/ቤት በአማርኛ እንጂ የኦሮሚኛ ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ለዚህ ነዉዋ አንዳንድ ሰዎች ድብቅ አጀንዳቸዉን በሆዳቸዉ ይዘዉ አማርኛ የሚነግስባት ባንዲት ኢትዮጵያ ስም የሚጮሁት! እኚህ ሰዎች እኩዕ ስራወቻቸዉን እንዳንረሳ ለምንድነዉ ክለሳ የሚሰጡን? የኦሮሞ ትግል የፈጠረዉ የቁቤ ትዉልድ እስካሌ ድረስ፣ በጣትም ሆኔ በጥይት ህልማቸዉ እዉን ሲለማይሆንና እንደበፊቱ አማርኛ የነገስባትና ኦሮሚኛም ሆነ ሌሎች ቋንቋዎች የሚጨቆኑባት እትዮጵያ ከእንግድህ ወዲህ ሊትፈጠር ሲለማትችል   ብዙም ሳይለፉ የህልም እንጀራቸዉን ወደ ጓዳቸዉ ቢመልሱት ይሻላቸኋል፡፡    
 
ይህ በእንድ እንዳሌ፣ሌላ ብሔር ወደ ኦሮሚያ መጥተዉ ከኦሮሚያ ስጠቀም፣ ኦሮሞ ደግሞ ከቤት ንብረቱ ስፈናቀል፤ ከድሮ ጀሚረዉ ከተለያየ ቦታ ለምሳሌ ለወንጂ ስኳር ፋብርካና ለሸንኮራ እርሻ ልማት ሰበብ የተፈናቀሉ የከረዩና የጂሌ ኦሮሞች፣በመንግስት እርሻ ልማት ሰበብ የተፈናቀሉ የአርሲና የባሌ ኦሮሞች፣ለከተማ ሲባል ከቀዬያቸዉና ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ የቱላማ ወይም የሸዋ ኦሮሞች፣ ከተለያየ ፋብርካ በሚወጣ መርዛማ ኬሚካሎች አከባብና ወንዞች  በተለይ አዲስ አባባ አከባቢ የሞጆ፣የአቃቂ፣የመቂንና ወዘተ  ሲመረዙ ማየት ይቻላል፡፡ ህሄንን በተመለከተ አቶ በቀለ ገርባ በ2002 ምርጫ ጊዜ የመድረክ ፓርቲን ወኪሎ ሲከራከሩ የነበሩ ይሄንኑ ነዉ በግልጽ ያስቀመጡት፡፡ እስት ማሰብ በሚችለዉ አእምሮ እናስብና፣ወያኔና ጀለወቹ እንደሚሉን ኦሮሞ እዉነትም ጸረ-ልማት ነዉ? እዉነት ብንናገር ለኢትዮጵያ ልማት እንደ ኦሮሞ የተጎዳ ማን ነዉ? ከብዙዎቹ ጉዳት አንድ ተጨባጪ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡ ብዙዎቻችን የሞጆ ከተማንና የሞጆ ወንዝን እናዉቃለን፡፡ ከአዳማ ወደ ሸገር-ፊንፊኔ ሲንመጣ  በሞጆ ከተማ ዉስጥ ሲናልፍ ትራንስፖርት ዉስጥ ሆነን ራሱ እዚያ በሚገኘዉ በቆዳ ፋብሪካ በተበከለ አየር ምክንያት ምን ያህል እንደሚንቸገር ብዙዎቻችን እናዉቃለን፡፡ አቶ በቀለ ገርባም እንዳሉ የተመረዙና ነፍስ የለላቸዉ ወንዞች እንደ ሞጆ፣አቃቂ፣መቂንና ወዘተ በተለይ በሸገር-ፊንፊኔ ዙሪያና ምስራቅ ሻዋ ዉስጥ በብዛት ይገኛሉ፡፡

በሸገር-ፊንፊኔ ዙሪያና በምስራቅ ሻዋ ዉስጥ የተመረዙት ወንዞች ለሰዉና ለእንስሳት መጠጥ ሲዉል ብዙ ሰዎችና እንስሰችም ሲሞቱ አፉ በዉሸት ልማት የተሸበበዉ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ሲሆኑ ከባህር ማዶ አልጄዚራ ነገሩን ሲሰማ እንደ አገር ቤቱ ሚዲያዎቹ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ሲላቃተዉ ባዳን የሚያሳዝን፣ ወገኑን ደገሞ የሚያቃጥል ፕሮግራም ሰረቶበታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ኢትዮጵያ ደህንነቶች  የአገሪቱን ምስጥር አዉጥተሃል በማለት እንዳስፈራሩት ጓደኛዬ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ነግሮኝ ነበር፡፡ አልጀዚራ ካነሳ ጉዳዮች ሁሉ አንጀቴን የበላኝ ሲለ ዓሚና በተሰብ ጉዳይ ነበረ፡፡ የቆቃ ወንዝ በመመረዝ ምክንያት ዓሚና ከባሏ ጭምር  6 ልጆቹዋን ቀብራለች፡፡ አሚና እንደሚትለዉ ህሄ ወንዝ ገዳይ ወንዝ ነዉ፡፡ ከ 9 ቤተሰቦቸዋ 7 አጥታለች፡፡ “ችግራችን የሚሰማንና የሚረዳን የበላይ አካልም ሲለለለን እ/ሄርን ብቻ ነዉ የሚንተማመነዉ” በማለት ዓሚና ለአልጀዚራ ተናገራለች፡፡ አልጄዚራ ይሄንን ፕሮገራም በሚሰራበት ወቅት ሃዳ ወራን ዎይም ባለቤቱን ቀብሮ ሀዘን ላይ የነበር  ከድር የተባሌ ገበሬ እንድ ሲል ለአልጀዚራ ተናገረዋል፡፡ “ባለቤተ በጉበት በሽታ ነች የሞተች፡፡ ለዚህ ያደረጋት ይህ የተበከለ ወንዝ መሆኑ ሀኪሞች ነግሮኛል፡፡ ሁለችንም ሆዳችን ዉስጥ ያመናል፡፡ ከምንሞት ብለን ነዉ ይሄንን የተበከለ ዉሃ የሚንጠጠዉ፡፡ በሽታ እየጠጣን መሆናችን እናዉቃለን፣ሆኖም ግን አማርጭ የለንም፡፡ ይህ የተበከለ ወንዝ ሰዉና የቤት እንስሳ እየገደለ መሆኑን ለመንግስት ብንነገረዉም የሚሰማን አጣን፡፡” 
     
ከአጼዎቹ ጊዜ ጀሚሮ በደቡብ ኦሮሚያ በጉጂ ዞን የሚትገኘዉን የአዶላና የሻኪሶ ወርቅ እያመረቱ አከባብዉ ግን ተበከለዉና ተጎሳቅለዉ ይገኛል፡፡ ዛሬም ብሆን በአዓመት ለ17 ዓመታት 4.5 ቶን ወይም 45 ኩንታል ወርቅ ከኦሮሚያ ከሻኪሶ  እየተመረተ በየወሩ በአዉሮፒላን እየተጫነ ነዉ ያለዉ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ብያስ 765 ኩንታል ወርቅ አምርቷል ማለት ነዉ፡፡እነርሱ እነ ሼክ አሊ አል ሙድ በአመት ከሻኪሾ  45 ኩንታል ወርቅ እናመርታለን አሉ እንጂ ከዚያ በላይና ብዙ ዓይነት ማዕድኖችን እንደሚያመርቱ ወስጥ አዋቂዎቹ ይናገራሉ፡፡ ኦሮሚያ ለኢትዮጵያ ልማት በእርሻ፣ በማዕድን፣ በእንስሳት እርባታ፣ በቆዳና ወዘተ የጀርባ አጥንት ሲትሆን ኦሮሞ ግን ምን ተጠቀሜ ለሚለዉን ጥያቄ እንስሳ ካልሆነ በስተቀር ማሰብ የሚችል ሁሉ ማንሳቱ አይቀረ ነዉ፡፡ አቶ በቀለ ገርባ በ2002 ምርጫ ጊዜ የመድረክ ፓርቲን ወኪሎ ሲከራከሩ በጉጂ ሻኪሾ አከባቢ በልማት ስም ግፍ እየተፈረ መሆኑ ሳያሳስቡ አላለፉም::
 
የኦሮሞ ሕዝብ ፀረ-ልማትም አይደለም፤እንዶዉም የኢትዮጵያ የልማት አባት ነዉ እንጂ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያ ልማት ሲል የተጎዳ አሳዳጊ እንድሁም  የዋህና ጥሩ አባት ነዉ፡፡ የዋህነት ግን ሞኝነት አይደለም፤አልፈዉም ተርፈዉ በኦሮሞ መሬት ላይ እየተቀመጠ ኦሮሞን እንደ ሞኝ የሚዘልፉ አልጠፉም፡፡  
 
በልማት ሥም፣ ዛሬም ብሆን ኦሮሞ መሬቱን እየአጣ ነዉ፤ ኦሮሞ እየተጎዳ ነው፡፡ ኦሮሞ ልማትን አይጠላም፡፡ የኦሮሞን ማንነት፣ቋንቋ፣ባህልና ወዘተን የሚያጠፋ ግን ይጠላል! ብዙ ገበሬዎች በእንቨስትመንት ስም በትንሽ ካሳ ከመሬታቸዉ የተነሱት ግን ተመልሰዉ የባለ ሀብቶቹ አሽከር እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. እራሱ በቀረጸዉ በፖሊሲ የሚለዉ  መሬቱ በገበሬ እጅ ስለሚገኝ መሬት ይሸጥ ይለመጥ ከተባሌ ገበሬዉ የባለብቶቸ አሽከር ሲለሚሆኑ፣ የመሬት ሽያጭ በኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. መቃብር ላይ ነዉ ይላሉ፡፡ ነገር ግን የኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. ካድሬዎች ያወጡትን ሕግ መልሰዉ እያፈረሱ ናቸዉ፡፡ በተለይ ወያኔዎቹ ብዙ ሀብት ካፈሩ በኋላ መሬት ይሸጥ ይለመጥ ይመስል በተለያዩ ቦታዎች በልማት ስም ገበሬዎቹን እያፈናቀሉ ለዉጪ ባለሀብቶች እየሸጡ ለራሳቸዉም መሬቱን እየወረሩ ናቸዉ፡፡ 
 
ከዚህ ጋርም በተያያዘ፣ ብሰሙ ኖሮ አቶ በቀለ ገርባ በ2002 ምርጫ ጊዜ የመድረክ ፓርቲን ወኪሎ ሲከራከሩ የኢትዮጵያ መንግስት መሬትን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉትን የአፍ መሸበብያ፣ ዉጪ አገር ያሉት ሰዎችን እንደ ማግነት መሳቢያ መሳሪያ እየሆኔ መምጣቱን ተናገሮ ነበረ፡፡
 
ሲለ መሬቱ ሲናነሳ በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር ልንገራችሁ፡፡ እኛ በተለይ ወጣቱ ትዉልድ በጣም ክፉ እድል ገጥሞናል፡፡ ብንማርም ትምህታችን በወያኔ ዘንድ ዋጋ አጣ፡፡ haadha haadha qaba taanaan intalli akkoo qabdii? ይላል አንድ የኦሮሚኛ ተረት፡፡ ትርጉምም እናቱዋ እናት ሲለሌላት ልጂቱዋ አያት ከዬት ታመጣለች? ድሮ የተማሬ ሰዉ ከተማ ዉስጥ ቤት እንድሰራ መሬት ይሰጠዋል፡፡ ዛሬ ግን ወያኔ እያሌ  ወጣቱ ትዉልድ ብያንስ 15 ዓመት በትምህርት ተቃትሎ ከወጣም  በኋላ በከተማ ዉስጥ የመኖሪያ መሬት አገኝተዉ ቤት መስራት ቀርቶ ተከራይቶ መኖር አይችልም፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ እዉነትም አቶ በቀሌ ገርባ እንደሚሉ መሬት የአፍ መሸበቢያና ሰዎችን ወደ ራሳቸዉ የሚሲቡበት መሳሪያ ነበረ፡፡ ጥቂቶቹ መሬትን እየቸበቸቡ ሚሊኔር ሆነዉ ተንደላቅቀዉ ሲኖሩ፣ ሰፊዉ ህዝብ ግን በደህነት ማቂ ተይዟል፡፡ ሁሉንም መሬቶች ከወረሩ በኋላ፣ የወረሩትን መሬቶች እንዴት ለራሳቸዉ ብቻ ሳይነቃባቸዉ ተጠቃሚ ለመሆን ከጥቂት ዓመታ በፊት የመሬት አሰጣጥ ቆመዋል በማለት አወጁ፡፡ ትንሽ ከቆዩ በኋላ መሬቱ በሊዚ በጨረታ ይሰጣል በማለት ብቅ አሉ፡፡ ማስተዋል ያለብን ሌላ ምስጥር በዛረዉ ጊዜ ገንዘብ ያለዉና መሬትን ተጫሪተዉ የመግዛትና የመዉሰድ አቅም ያለዉ ማን ነዉ? አንድ ባለስልጣን  በሸገር-ፊንፊኔ ዉስጥ 84 ቦታ በወረራ ሲይዝ፣ ይህ ድርጊት 84 ሚሊየን የኢትዮጵያን ህዝብ ቤት አልባ ያረገዋል፡፡ ከዚህ በመሬት ጉዳይ ጋር በተያያዜ በሆነ ጊዜ በኔ አቶ ደመቄ መኮንን በሚመራ የኢ.ህ.አ.ደ.ግ ባለስልጣን ልዑካን ቡድን አሜሪካ ዉስጥ በኢትዮጵያኖች እንደተሸማቃቁና በቅርብ ጊዜም  አቶ ረደዋን ሁሴን ሀገሩ ሰላም ነዉ ብለዉ አሜሪካ ዉስጥ ወደ አንዲት ሱቅ ገብተዉ እቃ ሲሸሚት በማዋረድ ስራ ቅስሙ ተሰብረዋል፡፡
 
 ኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. መቼ ነዉ የሚገባዉ?
 
ኢ.ሕ.አ.ደ.ግ.  የገባዉ ቢሆን ኖሮ፣ ዲሞኪራሳዊት ሀገር የሚኖሩና የራሳቸዉን እስትንፋስ የሚተነፍሱ የሆዳቸዉን እንደሚያወሩ ሁሉ፣ ባገር ቤት የሚኖሩ ሰዎችም፣ እስንፋሳቸዉን ሲለማይተነፉ በብዛት አዉጥተዉ አይናገሩም እንጂ አንጀታቸዉ እንዳረረ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡                         
 
ወደ መጀመሪያ ቁምነገረ ልመለስና፣ ቱባ ባለስጣኖቸሁና ጀለዎቹ ሁሉንም መሬቶች ከወረሩ በኋላ፣ የወረሩትን መሬቶች እንዴት ለራሳቸዉ ብቻ ሳይነቃባቸዉ ተጠቃሚ ለመሆን ከጥቂት ዓመታ በፊት የመሬት አሰጣጥ ቆመዋል በማለት ያወጁትን፣ ትንሽ ከቆዩ በኋላ መሬቱ በሊዚ በጨረታ ይሰጣል በማለት ብቅ አሉ፡፡ በተለይ ይህ የመሬት መቀራመት ወይም ወረራ በዲስ አበባ ባሉት በኦሮሚያ ከተሞች ከተካሄደ በኋላ በልማት ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት፣ የፊንፊኔ  ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ በአዲስ አበባ ስር ገብተዉ መልማት አለበት ብለዉ የልማት ተቆርቋሪ ሆነዉ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ከዚህ በፊትም የወያኔ መንግስት የአዳማ ከተማ የኦሮሞ ዋና ከተማ ነዉ ብለዉ ኦሮሞን ከአዲስ አበባ ሲያስወጣ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማረዎች ነቅተዉ ቢቃወሙም የገጠማቸዉ ግን መታሰርና ከትምህርታቸዉ መባርሩ ነበር፡፡ በሚገርም ሁኔታ ግን በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ምርጫዉን ሲያሸንፍ፣ ወያኔ ግን  “አዲስ አበባ አባት አላት፤የሀገሩ አባት ኦሮሞ ነዉ”  በማለት በእጁ የጠፈጠፈዉን ኦ.ሕ.ደ.ድ. ባንድ ማግስት ወደ አዲስ አበባ እንደመለሱ በነጋሪት ጠራ፡፡ 300 የሚሆኑ የኦሮሞ ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተባረሩትና የታሰሩት ተማሪዎች ከተጎዱ በኋላ እዉነት አገኙ ማለት ነዉ፡፡ የወያኔ መንግስት ይህን ያደረገበት  ዋንኛዉ ምክንያት፣ በአማራ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ መኃከል ጥላቻን በመዝራት እድሜዉን ለማዛረም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኦሮሞን ሲሰበስብ ለኦሮሞቹ ነፍጠኛ ተመልሰዉ ልመጣባችሁ ነዉ….ምናምንተ እያለ፣ አማራን ሲበሰብ ደግሞ  ለአማራዎቹ፣  እኔ ከሌለሁ ኦነግ ይመጣባቸኋልና ይበቀለቸኋል በማለት ያወናብዳል፡፡    
 
በኢ.ፈ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግስት አንቀጽ ፵፺/፶ (49/5) ላይ የሚለዉ፣ የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባ ልዪ ጥቅም ማግኘት አለበት ይላል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ እንኳን ልዪ ትቅም ከማግኘት ሌሎቹ ኢትዮጵያዉይን ያገኙት ጥቅም አላገኘም፡፡ ሲጀመር ራሱ አዲስ አባባ የማን ነች የሚል ነገር መቀመጥ ነበረበት፡፡  ከዚህ በፊትም የወያኔ መንግስት የአዳማ ከተማን የኦሮሞ ዋና ከተማ ነዉ ብለዉ ኦሮሞን ከአዲስ አበባ ሲያስወጣና  የዩኒቨርሲቲ ተማረዎች ነቅተዉ ቢቃወሙም፣ ኦ.ሕ.ደ.ድ ትዕዛዙን ተቀብሎ ሲሄድ፣  በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ሲያሸንፍ፣ ወያኔ  “አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፤ ሀገር አባት አላት፤የሀገሩ አባት ኦሮሞ ነዉ”  በማለት በእጁ የጠፈጠፈዉን ኦ.ሕ.ደ.ድ. ባንድ ማግስት ወደ አዲስ አበባ ስለ ጠራ፣ ይህ የፖሊትካ ቁማር ብዙዎችንና ወኔ ያላቸዉ ኦ.ሕ.ደ.ድ.ዎችን አናደድዉ ነበር፡፡ የወያኔ መንግስት  በልማት ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት የፊንፊኔ  ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ በአዲስ አበባ ስር አስገብቸ አለመለሁ ብለዉ፣ በልማት ስም የልማት ተቆርቋሪ ሆነዉ  በአዲስ አበባ ነገር ለ2ኛዉ ጊዜ ብቂ ሲል በብዙዎቹ ዘንድ ከዚህ በፍት በአዲስ አበባ ስም የተቆመረ ቁማር ትዝ ሲላቸዉ፣ ወያኔ ባልጠበቀ መልኩ እንኳን ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይቅርና ከአ.ሕ.ደ.ድ. አበላትም ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡
 
የወያኔ መንግስት በኦነግ ለይ በሰራ ሴራ፣ ኦነግን ከሀገር ካስወጣ በኋላ፣ አባት እንደሌላቸዉ ልጆች በኦሮሞ ህዝብ ከሀያ ዐመታት በላይ ብጫወትበትም፣ ኦነግ በቀረጸዉ ቁቤ ወይም ፊደል የተማርነዉ የቁቤ ትዉልደችና የተጨቆነ የኦሮሞ ህዝብ ሁሉ ሙሉ በሙሉ  ወደ ኦነግነት ተቀይሯል፡፡ ኦነግ ሀገር ዉስጥ የለም ብሎ ወያኔ ብጨፍርብንም ግድያ፣ እስራት፣ ጭቆና፣ ግርፋት፣ስደት፣ድህነትና ወዘተ ያማረራቸዉ  የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉና፣ በስተት በኦህደድ OPDO ላይ ተስፋ አድርገዉ እንድሁም ለዉጥ ሊያመጣልን ይችላል በማለት ለOPDO እድል ሰጥተዉት  የነበሩ ሁሉ  ለራሳቸዉ በራሳቸዉ ባሁኑ ጊዜ ወደ ኦነግነት ተለዉጧል፡፡ አቶ አባይ ፀሃዬ ይሄንኑም ሲላወቀ ነዉ ወሰለኝ አንዳንድ የኦ.ሕ.ደ.ድ. ባለስልጣኖችን  ልክ ለማስገባት የዛተባቸዉ፡፡ 
 
የወያኔ መንግስት ያሴረዉ ሴራ፣ በአዲስ አበባና በዲስ አባባ ከተሞች ልዩ ዞን ዙሪያ ብዙ ንብረት ሲላፈራ፣ የኦሮሞ ገበሬዎችን ከመሬታቸዉ እያፈናቀለ አዲስ አባባን ከሌላ ክልል ጋር በማገናኘት፣ አዲስ አበባን ከኦሮሞ ህዝብ እጅ በማዉጣት ኦሮሞና አማራን በማጋጨት እጁን ታጥቦ ለመብለት ተዘጋጅቷል፡፡ በተለይ ወያኔ አዲስ አበባን  በደብረ ብርሃን ከተማ በኩል ከአማራ ክልል ጋር በማገናኘት፣ከወሊሶም አሳልፈዉ ከጉራጌ ጋር በማያያዝ ኦሮሚያን በሁለት ቦታ በመክፈል አዲስ አበባን ከኦሮሚያ እጅ ለማዉጣት የተንኮል አጀንዳ እንደለዉ ተደርሰዉበታል፡፡  የወያኔ ሴራ ቀስ በቀስ  በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ከተሞችን ከኦሮሚያ ግዛት እያነጠቀ፣ ኦሮሚኛን የሚትገድልና አማርኛና ትግርኛን  የሚታወራ አዲስ አበባን ከደብረ ብርንና ከወልቂጤ  ጋር ማገናኘት ነበረ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ባለዉ አፉ፣ ወያኔ አዲስ አበባን ከአማራና ከደቡብ ክልሎች ጋር በማገናኘት ሸገር-ፊንፊኔ የኦሮሞ አይደለችም በማለት፣ እኛ ሲንባላ ለራሱ ዘና ብለዉ ለመኖር እንደፈለግ ታዉቋል፡፡
 
አንድ የኦሮሚኛ ተረት እንደምለዉ፣ “qoreen qoree hin waraantu, namni qoree lamaan wal-waraansisuuf yaale ofumaaf waraannama” ትርጉሙም፣ ሁለት እሾኮች አይወጋጉም፣ ሁለት እሾኮችን ለማወጋጋት የሞከረ ሰዉ ለራሱ ይወጋል ማለት ነዉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ማለት የሚፈልገዉ ነገር ቢኖር፣ በሰብዓዊ ሕሊና አማራና ኦሮሞ በወያኔ ሴራ በመንቃት አብረዉ የወያኔ መንግስት ለመጣልና ነጻነት ለማግኝት መታገል አለባቸዉ ባይ ነኝ፡፡ ኦሮሞ ሲጨፈጨፍ አማራ አይመለከተኝም ማለት የለበትም፡፡ አማራም ሲጨፈጨፍ ኦሮሞም ዝም ማለት የለበትም፡፡ የጋር ጠላታቸዉን በጋራ ብዋጉ የተሻሌ ይመስለኛል፡፡ ይህን ከላደረግን በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ዉስጥም የጥያቄያችን መልስ እንደሚናየዉ ጥይት ይሆናል፡፡ እዚህ ጋር መገንዘብ ያለበት ነገር ግን ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ስም ለአማራ የሚታገሉ፣ ለኦሮሞ ትግል ቦታ የማይሰጡም እንዳሉ መረሳት የለበትም፡፡እነዚህ ሰዎች ለትግላችን ቦታ ባይሰጡም፣እኛ አንጎዳም፣ ድሮም ደቦ አልለመንናቸዉም፡፡ ነግር ግን ለትግላችን ጥሩ ሀሳብ ቢኖራቸዉ ለራሳቸዉ ራሱ ጥቅም ነዉ፡፡ በነጻነታችን ቀንተዉ የሚሞቱ ሰዎች ካሉ ከወድሁ የሬሳ ሳጥን ቢያዘጋጁ መልከም ነዉ፡፡
 
የኦሮሞ ህዝብ ከድሮ ጀምሮ በተደራጀና በተናጠል እየታገለ ነዉ፡፡ በተለይ በቅርብ ጊዜ የወያኔ መንግስት፣ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተማዎች በተቀናጀ በጋራ ልማት ስም ያወጠዉ  ማሰተር ፕላኑ የኦሮሞን ህዝብና የኦሮሞን መሬት የሚያጠፋ ሲለሆነ በሚገርም ሁኔታ ተቋሞና ትግሉን አፏፏሜ፡፡በጣም የገረመኝ ነገር ሌላ ነግር ብኖር፣ በንጉሱ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  ያሰሙ የነበሩ መፈክርና በቅርቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሰሙት  መፈክር አንድ አይነት የመሆኑ ጉዳይ ነዉ፡፡ በንጉሱ ጊዜ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሬት ለአራሹ እያሉ ነበረ፤ በቅረቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገበሬዎች ከመሬታቸዉ እንዳይፈናቀሉ! መሬቱ የገበሬ ነዉ እያሉ ነበር፡ለመሆኑ ወዴት እያመራን ነን?
 
በዚያን ጊዜ ከተቀረጹት ፊልሞች መመልከት እንደ ቻልኩኝ፣ በንጉሱ ጊዜ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰለማዊ ሰልፍ ሲወጡ፣በዚያን ጊዜ የነበሩ ፖሊሶች ለተማርዎች የጥይት መልስ አልመለሱም፡፡ ዛሬ ግን ወያኔ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን የጥይት መልስ እየሰጠ፣ በጠራራ  ፀሃይ በ2014 በአምቦ፤በባሌ፣በጉደር፤በነቀምት፣ በሻምቡ፣በጊምብ፣በነጆ፣በአይራ፣በደምቢ ዶሎ፣በሴላሌና ወዘተ  በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድል፣ በጎንደር አከባብም 6 ሰዎችን ተኩሰዉ መግደሉ ተሰምተዋል፡፡ አንዳደም ወታደሮቹ ጦር ሜዳ መስሏቸዉ፣ በሰላማዊ ዜጎች ለይ የተኩስ እሩምታ ሲከፍቱ፣አገሪቱ በወታደሮች ብቻ ነዉ እነደ የሚትተዳደረዉ ያስብላል፡፡ በአምቦና በባሌ ሮቤ በመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎችና በነዋሪዎች ላይ በወያኔ  የተከፈተ የተኩስ እሩምታን የሰማ  ሰዉ፤ በምርጫ የወያኔ መንግስት መቀየር ዘበት እደሆነ ተገንዝቦ፣ ንብረቱን ሽጠዉ በስደትም የዓሳ እራት ከሚሆንና ከሰዉ አገር ተዋረደዉ ከመሞት በሚሰደድበት ገንዘብ  ጠበንጃን በመግዛት ከወያኔ ጋር ለመፋለም ይወስናል፡፡  
 
ሃሳቤን ባጭሩ ለመቋጨት፣ የኦሮሞ ሕዝብ ልማትን ጠልተዉ አይደለም የፊንፊኔ ዙሪያ የልዩ ዞን አዲስ አበባ ስር መግባትን የጠላ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ በኋላ የወያኔን ቃል የሚያምንበት ልብ አጥቷል፡፡ እስት ሕሊና ያለዉ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ከዚህ በፊት ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሰራዉን ተንኮል በማሰብ በኦሮሞ ቦታ ሆነዉ ይፍረድ! እኔ በበኩሌ አላምንም፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ እስር ቤቶች፣ በነርሱ ቋንቋ ማረሚያ ቤቶች 90 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች  የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነዉ ይባላል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የዋሕና ለሌሎች ሕዝቦች የሚራራና ከወንጀል ጋርም የሚያስተሳስረዉ ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያዉቃል፡፡ የወያኔ መንግስት ግን ኦሮሞን ሲለ ፈራ ብቻ፣ ስልጣን በጨበጠዉ አጋጣሚ ተጠቅሞ፣ በኦሮሞቹ ለይ የፈጸሜ ሴራ ሲያንሰዉ፣  ጨፍጭፈዉና አስረዉ መጨረስ አቅቶታል፡፡
 
የኦሮሞ ሕዝብ ልማትን አይጠላም፤እሺ እዉነትም፣ ነገሩ ለልማት ከሆነ፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞንን ከኦሮሚያ ክልል ማስተዳደር ሥር ለምን ማዉጣት ፈለጉ? ድረዉም ሁሉም ነገር በነርሱ ትዕዛዝ እንደሚከናዉን እናዉቃለን፡፡ ኦሮሚያ ሲር ሆና መልማት አትችልም ነበር? ኦሮሚያ ልማት ለይ አይደለችም ማለታቸዉ ነዉ? አንድ የኦሮሚኛ ተረት እንደሚለዉ፣ “bineensi bosona keessaa gugatu/fiigu kan ciisu kaasaa” ይላል፡፡ ትርጉሙም፣ከጫካ ዉስጥ ተነስቶ የሚሮጥ አዉሬ ሌላ የተኛዉን አዉሬ ያስነሳል ማለት ነዉ፡፡ ተረቱም እንደሚያሳየን በግድያ፣በእስራት፣በግርፊያ፣በመገልለ፣ፊትሕ በማጣት፣ በድህነት፡ በስራ አጥነት፣ ተምረዉ በመናቁና በወዘተ የተማረሩ የኦሮሞ ተወላጆች፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ከኦሮሚያ መስተዳደር ሥር እንድወጡና አዲስ አበባ ስር ማስገባት የተባለዉን ፒላን ለዩኒቭርሲቲ ተማርዎች  በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጥይት መልስ ሆነዉ ስለ ተመለሰላቸዉና  በወያኔ መንግስት የተማረረ ሕዝብ የተቃዉሞዉ ሰልፉን ወደ ሕዝባዊ አመጽ ቀይሮታል፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ አንዲነት ለፊትሕና ለዲሞኪራሲ ፓርቲ በ2014 በአዲስ አበባ ባደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እዳስታወቀ፣ የወያኔ መንግስት በኦሮሞቹ ላይ እያደረገ ያለዉ ጭፍጨፋ ያሳዘናቸዉና አጥብቀዉም እንደሚቃወሙ ገልጸዋል፡፡
 
የወያኔ መንግስት ከዚህ በፊትም አማራዎችን፣ አኟኮችን፣ጉሙዞችን፣ ደቡቦችን ፣አፋሮችን፣ሶመሌዎችንና ወዘተን ሰለጨፈጨፈ ፊትሕ የሚትፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ ባገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ የሚትገኝ ተጨቋኝ ህዝቦች ሁሉ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ቦታ የተጀመረ የኦሮሞን አመጽ በመደገፍ በወያኔ መንግስት ላይ ተቃዉሞዉችሁን እንዲታቀርቡ  ጥሪዬን አቀርባለሁኝ፡፡ ድል ለሰፍዉ ሕዝብ!