ባንደኛ
ደረጃ ኢትዮጵያን ልያጥፋትም ሆነ ልያኖራት የሚችለው የኦሮሞ ህዝብ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የኩሽ (የኢትዮጵያ) አባት ስለሆነ የኢትዮጵያን
አደራ በቀዳሚነት መውሰድ ያለበት እሱ ነው! ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ካሰኙት ብሄሮች ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብ
በሁሉም መስኮች የአንበሳ ድርሻ አለው። አሮሚያ ማንም ኢትዮጵያዊ በሰላም የሚኖርባትና ሰርቶ የሚለውጥባት ሀገር ናት። ለፖለቲካ
ፊጆታ ሲባል እንደሚባለው፣ የኦሮሞ ህዝብ ጠባብና ጎሴኛ ብሆንማ ኦሮሚያ ‘የኢትዮጵያ አውሮፓ ወይንም የኢትዮጵያ አሜሪካ’ አትሆንም
ነበረ። አሁን ከደረሱበት ስልጣኔያቸው ምክንያት በአውሮፓና በአሜሪካ፣
የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ይከበራል። የኦሮሞ ሕዝብ ደግም በአውሮፓውያንና በአሜሪካውያን በፊት የዲሞክራሲ መሠረት የሆነውን የገዳ
ሥርዓት ያለውና በገዳ ይተዳደር የነበረ አሁንም የገዳ ስርዓት ያለው ሕዝብ ነው። የኦሮሞ ድሞክራሲ(ገዳ ሥረዓት) ከግሪክ ድሞክራሲም
እንደምቀድም ተመስክሮለታል። የከግሪኮቹ ድሞክራሲ ባሪያና ሴቶችን አያሳትፊም ነበር። በኦሮሞ ድሞክራሲ(በገዳ ሥረዓት) ግን ባሪያ
የሚባል ነገር የለም፣ ሰው ሁሉ እኩል ነው።
የኦሮሞ ሕዝብ በቄኤው ላይ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋራ ተቻችሎ እንድሮር የገዳ ሥርዓትም መሠረት ጥሎላቸኋል። ከዬትኛውም
ከኢትዮጵያ ክልልች ሁሉ በይበልጥ ሁሉም ብሄር መጥቶበት በሰላም የሚኖርባትና ሰርቶ የሚለወጥባት ሀገር (ክልል) ኦሮሚያ ናት። በሌሎች
ክሎሎች ሌሎች ብሄሮች መኖር አይችሉም ማለቴ አይደለም። ለምሳሌ መቐሌ ብንሄድ በከተማም ሆነ በገጠርም ትግርኛና ትግሬ ብቻ ነው
የሚናገኘው። በተመሳሳይም ወደ ባሕርዳር ብንሄድ አማርኛና አማራን ነው የሚናገኘው። ወደ ኦሮሚያ ብንመጣ ግን እንኳን ትልቅ ከተማ
ቀርቶ ከትትንሾቹ ከተሞች ኦሮምኛና ኦሮሞን ብቻ አይደለም የሚናገኘው። ይህ ደግም ኦሮሞ እውነተኛው የኢትዮጵያ አባት መሆኑን ያስመሰክርለታል።
ኦሮሚያም እንደ ጥሩ እናት ሁሉንም ብሄሮች ሳታዳላ በእኩልነት አስተናገዳለች
ወይንም አሳደጋለች።
እንደ ወጋችንና ባህላችንም አባት የአባትነት ቦታ ፍቅርና ክብር ማግኝት ያስፈልጋል፣ ካልሆኔ ባሳደገው ልጆቹ ይፀፀትና ይረገማል። የአባት እርግማን ከዘር ወደ ዘር ይተላለፋል፣
የእናት ደግሞ ህይወትን ያቀጥፋል። ስለዚህ መሠረታዊና ወቅታዊ የኦሮሞ
ጥያቄ በቄኤዬ ላይ (ባገሬ) መሬቴ፣ቋንቋዬ፣ ባህሌ፣ንብረቴ፣እምነቴ፣መብቴ ወዘተ ይከበርልኝ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በቁመቴ ልክ
ልብስ ይሰፋልኝ ነው ዋንኛው ያሁኑ የኦሮሞ ጥያቄ... የኦሮሞ ሕዝብ ለራሱ በቻ ሳይሆን ለተጭቋኝ ህዝቦችም ጭምር ነው እየታገለ
ያለው። የኦሮሞ ጥያቄ የኢትዮጵያ ጥያቄ ነው! ሌሎች ተጨቋኝ ብሄሮችም ኢትዮጵያን ማዳን ከፈለጉ የኦሮሞን ህዝብ ትግል በጥርጣሬ
ዓይን ከማዬትና ዝም ብሎ ከመቀመጥ ይልቅ ወደ ትግሉ በመቀላቀል የትግሉን አካል መሆን ይጠበቅባቸኋል።
የኦሮሞ ሕዝብም ለኢትዮጵያ መሶሶ፣ ግንድና አባት እንደነረ
ለወደፊትም መሆን እንደምችል ‘ለኢትዮጵያ ሙግዚቶች’ ማሳያት ወይም ማሳመን መቻል አለባቸው። ወደድንም ጠላንም የዓለማችን ሃያል
ሀገሮች እንደ ኢትዮጵያ ያሉት ጨቅላ ሀገራትን በሙግዚት ነው የሚያስተዳድሩት። መግዚት እናት ለአደራ ወይንም ለጥቅም ነው እንጅ እንደ ወላድት እናት ሁሉም ችላ ህፃንን
አታሳድግም። ሕፃን ልጅ ለሙግዚት እናት ሲንሰጥ የሙግዚቷን ፍላጎት ማወቅ የግድ ይላል።
ያለ ኦሮሚያ ኢትዮጵያ እንደምታስነክስ የኢትዮጵያ ሙግዚቶች እንደሚያውቁ አውቃለሁ። ለዚህ ነው ባንደኛ ደረጃ የኢትዮጵያን
አደራ የአሮሞ ሕዝብ መውሰድ አለበት ያልኩኝ! ካንድ ሰው ሁለት ሰው
ይሻላል። ፍቅር ካለ ሁለት ሰዎች በመዋደድ በትዳር አንድ በመሆን ቤተሰብ ይመሰርታሉ። ፍቅር በመሃከላቸው ካለ ልጆችና ንብረት ባንድ
ላይ ያፈራሉ። መዋደድና መግባባት ካልቻሉና ከተካሰሱ ግን ፍርድ ቤት በህግ ይለያቸኋል። መለየት የጥላቻ ምልክት ነው! እንኳን ለሰው
ልጅ ቀርቶ ለእንስሳት ፍቅርን ከሰጠነው ጥሎን አይሄድም። ኦሮሞ ኢትዮጵያን እንደወደዳት ያይል ኢትዮጵያ ኦሮሞን ከወደደችሁ ኦሮሞና
ኢትዮጵያ ከቶ አይለያዩም! ስለዚህ ፍቅርን እንስበክ! ፍቅር ካለ ሁሉ አለ። ፍቅር ሁሌም አሸናፊ ነው።