Saturday, January 6, 2018

ሁሉም ብሄሮች በተሳተፉበት በድሮ ሥርዓት የአማራ ሕዝብ ብቻውን የሚወቀስበት ምክንያት የለም! “ከአያጅቦ ታሪክ” ቁራኛነት ተላቀን ከወያኔ እንላቀቅ!

ያለፈው አልፏል፣ ታሪክ ነው። ታሪክ እንደ ታሪክነት መጥፎም ጥሩም አለው። በድሮ ሥርዓት ውስጥ  አማራ ብቻውን ያደረገ አንድም ነገር የለም። ሁሉም ብሄሮች በሞላ ጎደል ተሳተፈውበታል፣ ልክ እንደ የዛሬው የወያኔ ሥርዓት።  ወያኔም ዛሬ እያኖረ ያለ ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ ከሶማሌ፣ ከአፋር፣ ከደቡብ፣ ወዘተ እያስተባበሩ ባላያችን ላይ እያስኖሩ መሆኑ ታርክ አይደለም ባይናችን የምናየው ነው። ወያኔ ትግሬ ብቻ አይደለም፣ የሥርዓቱ ተባባሪ ሁሉ ወያኔ ነው። ወያኔ ባጠፋ የትግራይ ሕዝብም መጠየ የለበትም።

ሕዝብና ሥርዓትን መለየት አስፈላጊ ነው። በተመሰሳይም ሁሉም ብሄሮች በተሳተፉበት በድሮ ሥርዓት የአማራ ሕዝብ ብቻውን የሚወቀስበት ምክንያት የለም። ሥርዓቱ  ለተወሰነ ብሄር ልያደላ ይችላል። ሆኖም ግን ሥርዓትና ሕዝብን መለየት አለብን። ወያኔም ዛሬ “ነፍጠኛ” እያለን የታሪክ ነቀርሳ ሆኖብናል። ወያኔ እራሱ ነፍጠኛ አይደለም ወይ? ነፍጠኛ ማለት በነፍጥ (በጠበንጃ)የገዛ ሰው እስከሆነ ድረስ ወያኔ እራሱ የዛሬ ነፍጠኛ ነው። ከትላንት ነፍጠኛ የሚለየው በይስሙላ ፌዴራሊዝም ሰዎች በራሳቸው ቋንቋ በመማራቸውና በመስራታቸው ብቻ ነው።   አምላክ አያደርገውና ከዚህ በኋል በነፍጥ የሚመጣም ካለ እርሱም ነፍጠኛ ነው!

በኢትዮጵያ የመንግስት ሥርዓት ታሪክ ውስጥ ዘርኝነትና የአገር ዝርፊያ በወያኔ ዘመን ነው ጣራ የነካ። የመንግስት ቁልፍ ቁልፍ ስልጣን እና የአገር ሀብት ከሚልሊክ ዘመን አንስቶ እስከ ደርግ መንግስት ድረስ መቼ በአንድ ብሄር ብቻ ተያዜ? በማን የመንግስት ዘመን ነው የኢትዮጵያኖች ክብር በመዋረድ አረቦች በሴት እህቶቻችን ላይ የተጫቱት እንዲሁም ሴቶቻችንና ወንዶቻችን የአረቦች ባሪያ የሆኑት?  ዬትኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ኢትዮጵያኖች ከመንግስታቸው ሲሸሹ በአሸባሪወች እንደ በግ የታሩዱና በባህርና በውቂያኖስ ውስጥ የዓሳ እራት የሆኑ?   ዬትኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው የብሄር ግጭት የምሰብክ ግጭቱን የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ የሚያደርግ ከወያኔ በስተቀር? 

ዬትኛው መንግስት ነው ጥላቻን እየሰበከ ጥላቻውን ደግሞ ሲንቅ በማድረግ የኖረበት ያለ ወያኔ በስተቀር? ዬትኛው መንግስት ነው የሕዝብ ለሕዝብ ቅርርብ ያንቦቀቦቀው ያለወያኔ በስተቀር? ዬትኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው የኢትዮጵያን ስልጣንና ሀብት በቤተሰብና በቤተዘመድ ተከፋፍሎ የገዛ ያለ ወያኔ በስተቀር? እና ወዘተ። አሁን ግን አዲስ ታሪክ እንስራና ታሪክን በበጎ እንለውጥ።  የታሪክ ነቀርሳ የሆነ ወያኔን አጥፍተን ታሪክ እንቀይር። ታሪካችን እንድቀና ወያኔ አይፈልግም። “ከአያጅቦ ታሪክ” ቁራኛነት ተላቀን ከወያኔ እንላቀቅ!


           በዳንኤል ባሪሶ አሬሪ ታህሳስ 7,2018 ዓ.ም.