ኢትዮጵያ ያለ
ሕዝቦቿ
ኢትዮጵያ
ልትባል
አትችልም!
ኢትዮጵያ የሰሜን አገራችን ክፍል፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና አማርኛ ቋንቋ ስላቀፈች ብቻ ኢትዮጵያ አትሆንም!
ኢትዮጵያ ማለት ሞላው ሕዝቦቿና መሬቶቿ ነው እንጂ የሰሜን አገራችን ክፍል፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና አማርኛ ቋንቋ ብቻ የሚትናገር አይደለችም! በመቶ በኢትዮጵያ ብር ኖቶች ላይ እንደሚናየው የአክሱም ሃውልት፣ የጎንደር የዓፄ ፋሲለደስ ቤተመንግስት፣ የኦርቶዶክስ ጳጳስ በድብቅ የተሰራ ምስል እና ወዘት ወደ ሰሜን አገራችን ክፍል እሴቶችን ብቻ እንደሚያሳዩ/እንደሚወክሉ ማስረጃ የሚሰጠን
ነው። የገዳ ስርዓትን የሚያሳይ አባ ገዳውስ ዬታለ? የኦርቶዶክስ ጳጳስ እንዳሳዩት የሙሲሊም ሼክ የታሌ? ከሰሜን
አገራችን
ክፍል በስተቀር ሌላ የኢትዮጵያ እሴቶች ዬታሉ?
“ከሰው በላይ ነኝ” ብሎ የሚያስብ ሰው የእኩልነት ወይም የደሞክራሲ ጥያቄ ሲነሳ ዉቃቢው ይነሳበታል። አንዳንድ ሰዎች ወይም ቡድኖች በድሮ
ስርዓት
የገነባች
ኢትዮጵያን አቆይቶ ለዘለዓለም ለማኖር ይፍጨረጭራሉ።
እነዚህ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች ካለ አማርኛ እና ካለ አረጓዴ ቢጫ ቀይ ቀላማት ባዲራና ምንም ነገር ሚዛን አይደፋላቸውም። አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በሄዱበት የአከባቢው ወይም የክልሉ የስራ ቋንቋ በአምቦ
ኦሮምኛ በመቀሌ ደግሞ ትግርኛ መናገራቸው እነዚህ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች “የአማርኛ መብት ተጥሰዋል” በማለት ኡ አሪ (ያዙኝ-ልቀቁኝ) እያሉ ናቸው። እነዚህ ሰዎች የአንድነት ኃይል ነን እያሉ ፀረ-አንድነት መሆናቸውን ያውቁ ይሆን? ዛሬም በትላንትናው ቦታ ባለንበት እንሂድ ነው ጫወታዉ?
“ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር” በማለትም ይጨፍራሉ ነገር ግን 80 ብሄር-ብሔረሰቦቿን ያላካተተች ኢትዮጵያ እንኳን ለዘለዓለም መኖር ቀርቶ ለ50 ዓመታት መኖር አትችልም። ኢትዮጵያ የ80 ብሄር ብሔረሰቦች ስብጥር ናት እንጂ የአንድና የሁለት ብሄር ባህል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ እሴት፣ ወዘተ አይደለችም።
ኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችን ሲታገል ቆይታለች። ኢትዮጵያ በተለይ የኦሮሞን ሕዝብ ካገለለች ሞቷን አፋጠነች። ከጥቂት ቡድኖች በስተቀረ አማርኛ ብቻ የምትናገር ኢትዮጵያ በድሮ አኳኻን ከቀጠለች የኢትዮጵያ እድሜ አጭር መሆኗ እራሷ ኢትዮጵያ የተረደች ትመስላለች። ለመስቀል ያልሆነች ቀሚስ ትበጣጠስ እንደተባለችም ኦሮሞንም ጨምሮ ለሌሎች ብሄር ያልሆነች ኢትዮጵያ….እናንተ
እራሳችሁ ባዶውን ቦታ ሙሉት።
ዳንኤል ባሪሶ አሬሪ
ነኝ።