እንደሚታወቀዉ
ከአጼ ምኒሊክ በፊት የዛረዉቱ ኢትዮጵያ የዛሬ ቅርጽ አልነበራትም፡፡ በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች ክልሎች ዉስጥ የሚገኙት ከተሞች አመሠራረታቸዉ ለነፍጠኞች ሠራዊቶች
ሲባል ከአዉሮፓ ባገኙት ነፍጥ (በዘመናዊ የጦር መሣሪያ) የአከባብን ሁኔታ ከቁጥጥራቸዉ ስር አስገብተዉ
ከሠፈሩበት በኋላ ነገሩ ከተመ ወይም ከተማ አሉት፡፡አጼ ምኒሊክ ለአዉሮፓዉያንና ለአሜርካዉያን የኢትዮጵያን ልጆች ለባሪያ
ንግድ በመሸጥ በለወጡት በጦር መሳሪያ ኦሮሞዎችን፣ ደቡቦችን፣አፋሮችን፣ሱማሌዎችንና ወዘተ በጦር መሳሪያ እየለወጡ፣ እንዲሁም ባገኙ
በጦር መሳሪያ፣ የተለያዩ የበፊቱ የኢትዮጵያን ግዛቶች እንደ ኦሮሞ፣አፋር፣ከፋ፣ዎላይታ፣ወዘተን
በመስበር የዛሬይቱ ኢትዮጵያን ፈጠሩት፡፡
የነፍጠኞች
ወታደሮች የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችን ለማስገበር ሲሉ ወደ ተለያዬ የኢትዮጵያ ክፍሌ አገሮች ዉስጥ ሲሰራጩ፣ የወታደሮች ካምፕ
ይመሰርቱ ነበረ፡፡ ነፍጠኞቹ ግዛታቸዉን ሲያከትሙ ነዉ ከተማን የመሰረቱት፡፡ በኦሮሚም ሆነ በሎሎች ክልሎች ዉስጥ ከተማ ሲከተም
በሃይል፣ በግዳጅ፣ በግድያ፣በቅሚያና በወዘተ ነዉ ከተማ የተከተመ፡፡ ነፍጠኞቹ ወደ ተለያዬ የኢትዮጵያ ክፍሌ አገሮች ዉስጥ ሲሰራጩ
የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይም የነበሩ፤በፊዉዳሊዚም ጊዜም ገበሬ ከሚያርሰዉ ምርት 1/3 ለኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን የሚሰጥ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ አማርኛ ቋንቋ በብዛት በኢትዮጵያ ከተሞች ዉስጥ ለሚነገርበት ዋነኛዉ ምክንያትም ይህ
ሆነዉ ነዉ እንጂ የቋንቋዎች ንጉስ ሆነዉ አይደለም፡፡
መታየት
ያለበት ሌለ ጉዳይ ደግሞ በተለይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በጉሙዝና በወዘተ ዙሪያ የሚገኙ ከተሞቸ ዉስት በብዛት የሚኖሩ የአከባብ ተወላጆች አይደሉም፡፡ ዛሬም
ብሆን በእነኚ የክልል ከተሞች ዉስጥ በብዛት የሚነገረዉ ቋንቋም አማርኛ ነዉ፡፡ አማሪኛ ለምን ተነገሬ ማለቴ አይደለም፤ ቋንቋ ሀብት
ነዉና፡፡ እኔም አማርኛ በመቻሌ ነዉ ሀሳቤን በአማሪኛ እየገለጽኩኝ ያለሁት፡፡ ዋና ቁምነ ገሩ ግን ማንኛዉም ሰዉ ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራት፣መጉበኘትና ወዘተ ይችላል፡፡ ይህ ሰዉ ግን ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራትና መጉበኘት የሚችለዉ
የአከባቢዉን ሕብረተሰብ ቋንቋንና ባህልን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ዛሬ ግን በሌሎችም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የሚናየዉ ነገር
በጣም የሚገርም ነዉ፡፡ በአጼዎች ጊዜ አማርኛ እንደ የንጉስ ቋንቋ ተወስደዉ፣ ሌላዎቹን ግን የማንቋሸሽና የመናቅ አዝማሚያ ይታይ
ነበረ፡፡ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋትም ሆነ በብሄር ብዛት ኦሮሚያና ኦሮሞ መሆኑን የሚክድ ሰዉ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሆነዉም ግን የኦሮሞ
ህዝብ ከአጼዎች ዘመን ጀሚሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከስርዓቱም ሆነ ከከተማ ያገኘ ጥቅም የለም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ያገኘ ነገር ብነገር
ከቦታ መፈናቀል፣ተመልሰዉ አገልጋያቸዉ መሆን፣የራሱን ቋንቋ ማጣት፣ሳይወድ በገዛ አገሩ የሌለ ብሄር ቋንቋና ባህል መቀበል
(assimilation) ና የመሳሰሉት ግፎች ደርሶበታል፡፡ እዚህ ላይ የቀዲሞ የኢትዮጵያ የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በዲሮና በአሁኑ ስርዓት በኦሮሞች ላይ የተፈጸሙትና አሁንም እየተፈጸሙ ላሉት ግፎች የሚዘገንን ሲለመሆኑ ለኢሳት
ቴሌቪዥን በ2014 በሰጠ አስተያየት፣ ከወያኔ ጋር በሰራባቸዉ ጥቂት
ዓመታት ዉስጥ ለሪልስቴቶች ብቻ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከ29 የገጠር
ቀበሌዎች 150.000 (መቶ ሃምሳ ሺህ) ኦሮሞዎች ተፈናቅለዉ የገቡበት
አይታወቅም ብሏል፡፡ ኦሮሞቹን አፈናቅለዉ እንደ ሀያት ሪልስቴቶች
የሰሩት የወያኔ ቱባ ባለስልጣኖች መሆናቸዉን አቶ ኤርሚያስ በጠሰዉ ቃለ-ምልልስ ተናግሯል፡፡
ከተማንና
ኦሮሞን በተመለከተ ሌላ ግፍ፣የሚገርም ነገር ብኖር፣ እኔ ራሴ በአይኔ ያየሁት ነገር፣ አንዳንድ በኦሮሚያ ከተሞች ዉስጥ የተወለዱት
ልጆች ኦሮሚኛ አለመቻላቸዉ ሳይሆን የገረመኝ፣እናት አማርኛ አትችልም፤ ልጇ ደገሞ ኦሮሚኛ አትችልም፡፡ እንደዚህ አይነቱ የተዛባ
ህብረተሰብ እስከ መቼ ነዉ የሚንፈጥረዉ? ግን ለምንድ ነዉ በኦሮሞና
በኦሮሚኛ ላይ የማጥፋት ዘመቻ የሚከፈተዉ? በኦሮሚያ እንብርት በሸገር-ፊንፊኔ
ከተማ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተንቀዉ የዉጪ ሀገር ቋንቋዎች እንደ ፈረሳይኛና አረብኛ በትምህርት መልክም ይሰጣል፣ በብዙሃን መገናኛም ይነገራል፡፡
ኦሮሞ ይሄንን አይቶ ልክ አይደለም ብለዉ ተቃዉሞ ሲያቀርብ ምኑነዉ ጥፋቱ፣ ምኑነዉ ጠባብነቱ? ወያኔም የራሱን ቋንቋ ከጉዳት ሲያድነዉ
ኦሮሞኛን ኣባ ካና አላለም፡፡ ወያኔ ወደ ስልጣን ሲመጣ በመቀሌ ከተማ ራሱ ትግርኛ ጠፈቶ በአማሪኛ ተተክቶ እንደነበረና ከዚያ በኋላ
ወያኔ በዱላ ማስመለሱንና ዛሬ ግን አማርኛ በትገራይ ክልልም ሆነ በመቀሌ ከተማ እንግዳ መሆኑን እኔ ራሴ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በሚማርበት
ጊዜ ሰምቸም አይቼ ነበረ፡፡
ከላይ
እንደ ጠቀስኩኝ ሁሉ፣ አሁንም ደገሜ እላለሁኝ፤ ማንኛዉም ሰዉ ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራት፣መጉበኘትና ወዘተ ይችላል፡፡ በሰላማዊና በሰነጠለ ዓዕምሮ ሲናይ ይህ ሰዉ ግን ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራትና
መጉበኘት የሚችለዉ፣ የአከባቢዉን ሕብረተሰብ ቋንቋንና ባህልን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ በኦሮሚያ እያየን ያለነዉ ነግር
ይሄን የሚቃረን ነዉ፡፡ እዉነት ብንናገር እኮ አሪፍ ነዉ! ሌሎች ብሄር በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች ክልሎች ሲኖሩ በነርሱ ቋንቋና ባህል
ሊያስተዳደሩን አይችሉም፤እንድሁም ቋንቋችንና ባህላችንን ማጥፋትና መግደል የለባቸዉም፡፡ በባሕር ዳር፣ በጎንደርና በጎጀም በብዛት
የሚኖረዉ ኦሮሞ ነዉ ወይስ አማራ ወይስ ትግሬ? በመቀሌ፣በአድዋና የመሳሰሉ ከተሞች ዉስጥ የኦሮሞ ህዝብ በነዋሪነት ይኖራልን? ወደ
ኦሮሚያ ስንመጣስ፣ በሸገር፣በአዳማ፣በሻሻማኔ፣በአሰላ፣በድሬ ዳዋ፣ በነቀምት፣ በአዶላ፣ በጭሮ፣በያቤሎና በወዘተ የአማራ፣የትግሬ፣የደቡብ
ብሄር ነዋሪ ብቆጠር እነርሱ ናቸዉ ወይስ ኦሮሞ ነዉ የሚበልጠዉ? አሁንም የሚገርማቹ ነገር፣ በብዙ የኦሮሚያ ከተሞች ዉስጥ የመዋለ-ሕጻናት
ት/ቤት በአማርኛ እንጂ የኦሮሚኛ ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ለዚህ ነዉዋ አንዳንድ ሰዎች ድብቅ አጀንዳቸዉን በሆዳቸዉ ይዘዉ አማርኛ
የሚነግስባት ባንዲት ኢትዮጵያ ስም የሚጮሁት! እኚህ ሰዎች እኩዕ ስራወቻቸዉን እንዳንረሳ ለምንድነዉ ክለሳ የሚሰጡን? የኦሮሞ ትግል
የፈጠረዉ የቁቤ ትዉልድ እስካሌ ድረስ፣ በጣትም ሆኔ በጥይት ህልማቸዉ እዉን ሲለማይሆንና እንደበፊቱ አማርኛ የነገስባትና ኦሮሚኛም
ሆነ ሌሎች ቋንቋዎች የሚጨቆኑባት እትዮጵያ ከእንግድህ ወዲህ ሊትፈጠር ሲለማትችል ብዙም ሳይለፉ የህልም እንጀራቸዉን ወደ ጓዳቸዉ ቢመልሱት ይሻላቸኋል፡፡
ይህ
በእንድ እንዳሌ፣ሌላ ብሔር ወደ ኦሮሚያ መጥተዉ ከኦሮሚያ ስጠቀም፣ ኦሮሞ ደግሞ ከቤት ንብረቱ ስፈናቀል፤ ከድሮ ጀሚረዉ ከተለያየ
ቦታ ለምሳሌ ለወንጂ ስኳር ፋብርካና ለሸንኮራ እርሻ ልማት ሰበብ የተፈናቀሉ የከረዩና የጂሌ ኦሮሞች፣በመንግስት እርሻ ልማት ሰበብ
የተፈናቀሉ የአርሲና የባሌ ኦሮሞች፣ለከተማ ሲባል ከቀዬያቸዉና ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ የቱላማ ወይም የሸዋ ኦሮሞች፣ ከተለያየ ፋብርካ
በሚወጣ መርዛማ ኬሚካሎች አከባብና ወንዞች በተለይ አዲስ አባባ አከባቢ
የሞጆ፣የአቃቂ፣የመቂንና ወዘተ ሲመረዙ ማየት ይቻላል፡፡ ህሄንን በተመለከተ
አቶ በቀለ ገርባ በ2002 ምርጫ ጊዜ የመድረክ ፓርቲን ወኪሎ ሲከራከሩ የነበሩ ይሄንኑ ነዉ በግልጽ ያስቀመጡት፡፡ እስት ማሰብ
በሚችለዉ አእምሮ እናስብና፣ወያኔና ጀለወቹ እንደሚሉን ኦሮሞ እዉነትም ጸረ-ልማት ነዉ? እዉነት ብንናገር ለኢትዮጵያ ልማት እንደ
ኦሮሞ የተጎዳ ማን ነዉ? ከብዙዎቹ ጉዳት አንድ ተጨባጪ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡ ብዙዎቻችን የሞጆ ከተማንና የሞጆ ወንዝን እናዉቃለን፡፡
ከአዳማ ወደ ሸገር-ፊንፊኔ ሲንመጣ በሞጆ ከተማ ዉስጥ ሲናልፍ ትራንስፖርት
ዉስጥ ሆነን ራሱ እዚያ በሚገኘዉ በቆዳ ፋብሪካ በተበከለ አየር ምክንያት ምን ያህል እንደሚንቸገር ብዙዎቻችን እናዉቃለን፡፡ አቶ
በቀለ ገርባም እንዳሉ የተመረዙና ነፍስ የለላቸዉ ወንዞች እንደ ሞጆ፣አቃቂ፣መቂንና ወዘተ በተለይ በሸገር-ፊንፊኔ ዙሪያና ምስራቅ
ሻዋ ዉስጥ በብዛት ይገኛሉ፡፡
በሸገር-ፊንፊኔ
ዙሪያና በምስራቅ ሻዋ ዉስጥ የተመረዙት ወንዞች ለሰዉና ለእንስሳት መጠጥ ሲዉል ብዙ ሰዎችና እንስሰችም ሲሞቱ አፉ በዉሸት ልማት
የተሸበበዉ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ሲሆኑ ከባህር ማዶ አልጄዚራ ነገሩን ሲሰማ እንደ አገር ቤቱ
ሚዲያዎቹ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ሲላቃተዉ ባዳን የሚያሳዝን፣ ወገኑን ደገሞ የሚያቃጥል ፕሮግራም ሰረቶበታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ፣
ኢትዮጵያ ደህንነቶች የአገሪቱን ምስጥር አዉጥተሃል በማለት እንዳስፈራሩት
ጓደኛዬ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ነግሮኝ ነበር፡፡ አልጀዚራ ካነሳ ጉዳዮች ሁሉ አንጀቴን የበላኝ ሲለ ዓሚና በተሰብ ጉዳይ ነበረ፡፡
የቆቃ ወንዝ በመመረዝ ምክንያት ዓሚና ከባሏ ጭምር 6 ልጆቹዋን ቀብራለች፡፡
አሚና እንደሚትለዉ ህሄ ወንዝ ገዳይ ወንዝ ነዉ፡፡ ከ 9 ቤተሰቦቸዋ 7 አጥታለች፡፡ “ችግራችን የሚሰማንና የሚረዳን የበላይ አካልም
ሲለለለን እ/ሄርን ብቻ ነዉ የሚንተማመነዉ” በማለት ዓሚና ለአልጀዚራ ተናገራለች፡፡ አልጄዚራ ይሄንን ፕሮገራም በሚሰራበት ወቅት
ሃዳ ወራን ዎይም ባለቤቱን ቀብሮ ሀዘን ላይ የነበር ከድር የተባሌ
ገበሬ እንድ ሲል ለአልጀዚራ ተናገረዋል፡፡ “ባለቤተ በጉበት በሽታ ነች የሞተች፡፡ ለዚህ ያደረጋት ይህ የተበከለ ወንዝ መሆኑ ሀኪሞች
ነግሮኛል፡፡ ሁለችንም ሆዳችን ዉስጥ ያመናል፡፡ ከምንሞት ብለን ነዉ ይሄንን የተበከለ ዉሃ የሚንጠጠዉ፡፡ በሽታ እየጠጣን መሆናችን
እናዉቃለን፣ሆኖም ግን አማርጭ የለንም፡፡ ይህ የተበከለ ወንዝ ሰዉና የቤት እንስሳ እየገደለ መሆኑን ለመንግስት ብንነገረዉም የሚሰማን
አጣን፡፡”
ከአጼዎቹ
ጊዜ ጀሚሮ በደቡብ ኦሮሚያ በጉጂ ዞን የሚትገኘዉን የአዶላና የሻኪሶ ወርቅ እያመረቱ አከባብዉ ግን ተበከለዉና ተጎሳቅለዉ ይገኛል፡፡
ዛሬም ብሆን በአዓመት ለ17 ዓመታት 4.5 ቶን ወይም 45 ኩንታል ወርቅ ከኦሮሚያ ከሻኪሶ እየተመረተ በየወሩ በአዉሮፒላን እየተጫነ ነዉ ያለዉ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ
ብያስ 765 ኩንታል ወርቅ አምርቷል ማለት ነዉ፡፡እነርሱ እነ ሼክ አሊ አል ሙድ በአመት ከሻኪሾ 45 ኩንታል ወርቅ እናመርታለን አሉ እንጂ ከዚያ በላይና ብዙ ዓይነት ማዕድኖችን
እንደሚያመርቱ ወስጥ አዋቂዎቹ ይናገራሉ፡፡ ኦሮሚያ ለኢትዮጵያ ልማት በእርሻ፣ በማዕድን፣ በእንስሳት እርባታ፣ በቆዳና ወዘተ የጀርባ
አጥንት ሲትሆን ኦሮሞ ግን ምን ተጠቀሜ ለሚለዉን ጥያቄ እንስሳ ካልሆነ በስተቀር ማሰብ የሚችል ሁሉ ማንሳቱ አይቀረ ነዉ፡፡ አቶ
በቀለ ገርባ በ2002 ምርጫ ጊዜ የመድረክ ፓርቲን ወኪሎ ሲከራከሩ በጉጂ ሻኪሾ አከባቢ በልማት ስም ግፍ እየተፈረ መሆኑ ሳያሳስቡ
አላለፉም::
የኦሮሞ
ሕዝብ ፀረ-ልማትም አይደለም፤እንዶዉም የኢትዮጵያ የልማት አባት ነዉ እንጂ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያ ልማት ሲል የተጎዳ አሳዳጊ
እንድሁም የዋህና ጥሩ አባት ነዉ፡፡ የዋህነት ግን ሞኝነት አይደለም፤አልፈዉም
ተርፈዉ በኦሮሞ መሬት ላይ እየተቀመጠ ኦሮሞን እንደ ሞኝ የሚዘልፉ አልጠፉም፡፡
በልማት
ሥም፣ ዛሬም ብሆን ኦሮሞ መሬቱን እየአጣ ነዉ፤ ኦሮሞ እየተጎዳ ነው፡፡ ኦሮሞ ልማትን አይጠላም፡፡ የኦሮሞን ማንነት፣ቋንቋ፣ባህልና
ወዘተን የሚያጠፋ ግን ይጠላል! ብዙ ገበሬዎች በእንቨስትመንት ስም በትንሽ ካሳ ከመሬታቸዉ የተነሱት ግን ተመልሰዉ የባለ ሀብቶቹ
አሽከር እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. እራሱ በቀረጸዉ በፖሊሲ የሚለዉ
መሬቱ በገበሬ እጅ ስለሚገኝ መሬት ይሸጥ ይለመጥ ከተባሌ ገበሬዉ የባለብቶቸ አሽከር ሲለሚሆኑ፣ የመሬት ሽያጭ በኢ.ሕ.አ.ደ.ግ.
መቃብር ላይ ነዉ ይላሉ፡፡ ነገር ግን የኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. ካድሬዎች ያወጡትን ሕግ መልሰዉ እያፈረሱ ናቸዉ፡፡ በተለይ ወያኔዎቹ ብዙ
ሀብት ካፈሩ በኋላ መሬት ይሸጥ ይለመጥ ይመስል በተለያዩ ቦታዎች በልማት ስም ገበሬዎቹን እያፈናቀሉ ለዉጪ ባለሀብቶች እየሸጡ ለራሳቸዉም
መሬቱን እየወረሩ ናቸዉ፡፡
ከዚህ
ጋርም በተያያዘ፣ ብሰሙ ኖሮ አቶ በቀለ ገርባ በ2002 ምርጫ ጊዜ የመድረክ ፓርቲን ወኪሎ ሲከራከሩ የኢትዮጵያ መንግስት መሬትን
ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉትን የአፍ መሸበብያ፣ ዉጪ አገር ያሉት ሰዎችን እንደ ማግነት መሳቢያ መሳሪያ እየሆኔ መምጣቱን ተናገሮ ነበረ፡፡
ሲለ
መሬቱ ሲናነሳ በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር ልንገራችሁ፡፡ እኛ በተለይ ወጣቱ ትዉልድ በጣም ክፉ እድል ገጥሞናል፡፡ ብንማርም ትምህታችን
በወያኔ ዘንድ ዋጋ አጣ፡፡ haadha haadha qaba taanaan intalli akkoo qabdii? ይላል አንድ የኦሮሚኛ
ተረት፡፡ ትርጉምም እናቱዋ እናት ሲለሌላት ልጂቱዋ አያት ከዬት ታመጣለች? ድሮ የተማሬ ሰዉ ከተማ ዉስጥ ቤት እንድሰራ መሬት ይሰጠዋል፡፡
ዛሬ ግን ወያኔ እያሌ ወጣቱ ትዉልድ ብያንስ 15 ዓመት በትምህርት
ተቃትሎ ከወጣም በኋላ በከተማ ዉስጥ የመኖሪያ መሬት አገኝተዉ ቤት
መስራት ቀርቶ ተከራይቶ መኖር አይችልም፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ እዉነትም አቶ በቀሌ ገርባ እንደሚሉ መሬት የአፍ መሸበቢያና ሰዎችን
ወደ ራሳቸዉ የሚሲቡበት መሳሪያ ነበረ፡፡ ጥቂቶቹ መሬትን እየቸበቸቡ ሚሊኔር ሆነዉ ተንደላቅቀዉ ሲኖሩ፣ ሰፊዉ ህዝብ ግን በደህነት
ማቂ ተይዟል፡፡ ሁሉንም መሬቶች ከወረሩ በኋላ፣ የወረሩትን መሬቶች እንዴት ለራሳቸዉ ብቻ ሳይነቃባቸዉ ተጠቃሚ ለመሆን ከጥቂት ዓመታ
በፊት የመሬት አሰጣጥ ቆመዋል በማለት አወጁ፡፡ ትንሽ ከቆዩ በኋላ መሬቱ በሊዚ በጨረታ ይሰጣል በማለት ብቅ አሉ፡፡ ማስተዋል ያለብን
ሌላ ምስጥር በዛረዉ ጊዜ ገንዘብ ያለዉና መሬትን ተጫሪተዉ የመግዛትና የመዉሰድ አቅም ያለዉ ማን ነዉ? አንድ ባለስልጣን በሸገር-ፊንፊኔ ዉስጥ 84 ቦታ በወረራ ሲይዝ፣ ይህ ድርጊት 84 ሚሊየን
የኢትዮጵያን ህዝብ ቤት አልባ ያረገዋል፡፡ ከዚህ በመሬት ጉዳይ ጋር በተያያዜ በሆነ ጊዜ በኔ አቶ ደመቄ መኮንን በሚመራ የኢ.ህ.አ.ደ.ግ
ባለስልጣን ልዑካን ቡድን አሜሪካ ዉስጥ በኢትዮጵያኖች እንደተሸማቃቁና በቅርብ ጊዜም አቶ ረደዋን ሁሴን ሀገሩ ሰላም ነዉ ብለዉ አሜሪካ ዉስጥ ወደ አንዲት ሱቅ
ገብተዉ እቃ ሲሸሚት በማዋረድ ስራ ቅስሙ ተሰብረዋል፡፡
ኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. መቼ ነዉ የሚገባዉ?
ኢ.ሕ.አ.ደ.ግ. የገባዉ ቢሆን ኖሮ፣ ዲሞኪራሳዊት ሀገር የሚኖሩና የራሳቸዉን እስትንፋስ የሚተነፍሱ
የሆዳቸዉን እንደሚያወሩ ሁሉ፣ ባገር ቤት የሚኖሩ ሰዎችም፣ እስንፋሳቸዉን ሲለማይተነፉ በብዛት አዉጥተዉ አይናገሩም እንጂ አንጀታቸዉ
እንዳረረ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
ወደ
መጀመሪያ ቁምነገረ ልመለስና፣ ቱባ ባለስጣኖቸሁና ጀለዎቹ ሁሉንም መሬቶች ከወረሩ በኋላ፣ የወረሩትን መሬቶች እንዴት ለራሳቸዉ ብቻ
ሳይነቃባቸዉ ተጠቃሚ ለመሆን ከጥቂት ዓመታ በፊት የመሬት አሰጣጥ ቆመዋል በማለት ያወጁትን፣ ትንሽ ከቆዩ በኋላ መሬቱ በሊዚ በጨረታ
ይሰጣል በማለት ብቅ አሉ፡፡ በተለይ ይህ የመሬት መቀራመት ወይም ወረራ በዲስ አበባ ባሉት በኦሮሚያ ከተሞች ከተካሄደ በኋላ በልማት
ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ
በአዲስ አበባ ስር ገብተዉ መልማት አለበት ብለዉ የልማት ተቆርቋሪ ሆነዉ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ከዚህ በፊትም የወያኔ መንግስት የአዳማ
ከተማ የኦሮሞ ዋና ከተማ ነዉ ብለዉ ኦሮሞን ከአዲስ አበባ ሲያስወጣ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማረዎች ነቅተዉ ቢቃወሙም የገጠማቸዉ ግን መታሰርና
ከትምህርታቸዉ መባርሩ ነበር፡፡ በሚገርም ሁኔታ ግን በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ምርጫዉን ሲያሸንፍ፣ ወያኔ
ግን “አዲስ አበባ አባት አላት፤የሀገሩ አባት ኦሮሞ ነዉ” በማለት በእጁ የጠፈጠፈዉን ኦ.ሕ.ደ.ድ. ባንድ ማግስት ወደ አዲስ አበባ
እንደመለሱ በነጋሪት ጠራ፡፡ 300 የሚሆኑ የኦሮሞ ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተባረሩትና የታሰሩት ተማሪዎች ከተጎዱ በኋላ
እዉነት አገኙ ማለት ነዉ፡፡ የወያኔ መንግስት ይህን ያደረገበት ዋንኛዉ
ምክንያት፣ በአማራ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ መኃከል ጥላቻን በመዝራት እድሜዉን ለማዛረም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኦሮሞን ሲሰበስብ ለኦሮሞቹ
ነፍጠኛ ተመልሰዉ ልመጣባችሁ ነዉ….ምናምንተ እያለ፣ አማራን ሲበሰብ ደግሞ
ለአማራዎቹ፣ እኔ ከሌለሁ ኦነግ ይመጣባቸኋልና ይበቀለቸኋል
በማለት ያወናብዳል፡፡
በኢ.ፈ.ዲ.ሪ.
ሕገ-መንግስት አንቀጽ ፵፺/፶ (49/5) ላይ የሚለዉ፣ የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባ ልዪ ጥቅም ማግኘት አለበት ይላል፡፡ የኦሮሞ
ህዝብ እንኳን ልዪ ትቅም ከማግኘት ሌሎቹ ኢትዮጵያዉይን ያገኙት ጥቅም አላገኘም፡፡ ሲጀመር ራሱ አዲስ አባባ የማን ነች የሚል ነገር
መቀመጥ ነበረበት፡፡ ከዚህ በፊትም የወያኔ መንግስት የአዳማ ከተማን
የኦሮሞ ዋና ከተማ ነዉ ብለዉ ኦሮሞን ከአዲስ አበባ ሲያስወጣና የዩኒቨርሲቲ
ተማረዎች ነቅተዉ ቢቃወሙም፣ ኦ.ሕ.ደ.ድ ትዕዛዙን ተቀብሎ ሲሄድ፣
በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ሲያሸንፍ፣ ወያኔ “አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፤ ሀገር አባት አላት፤የሀገሩ አባት ኦሮሞ ነዉ” በማለት በእጁ የጠፈጠፈዉን ኦ.ሕ.ደ.ድ. ባንድ ማግስት ወደ አዲስ አበባ
ስለ ጠራ፣ ይህ የፖሊትካ ቁማር ብዙዎችንና ወኔ ያላቸዉ ኦ.ሕ.ደ.ድ.ዎችን አናደድዉ ነበር፡፡ የወያኔ መንግስት በልማት ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ በአዲስ አበባ ስር አስገብቸ አለመለሁ ብለዉ፣
በልማት ስም የልማት ተቆርቋሪ ሆነዉ በአዲስ አበባ ነገር ለ2ኛዉ
ጊዜ ብቂ ሲል በብዙዎቹ ዘንድ ከዚህ በፍት በአዲስ አበባ ስም የተቆመረ ቁማር ትዝ ሲላቸዉ፣ ወያኔ ባልጠበቀ መልኩ እንኳን ከዩኒቨርሲቲ
ተማሪዎች ይቅርና ከአ.ሕ.ደ.ድ. አበላትም ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡
የወያኔ
መንግስት በኦነግ ለይ በሰራ ሴራ፣ ኦነግን ከሀገር ካስወጣ በኋላ፣ አባት እንደሌላቸዉ ልጆች በኦሮሞ ህዝብ ከሀያ ዐመታት በላይ
ብጫወትበትም፣ ኦነግ በቀረጸዉ ቁቤ ወይም ፊደል የተማርነዉ የቁቤ ትዉልደችና የተጨቆነ የኦሮሞ ህዝብ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ኦነግነት ተቀይሯል፡፡ ኦነግ ሀገር ዉስጥ የለም ብሎ ወያኔ ብጨፍርብንም
ግድያ፣ እስራት፣ ጭቆና፣ ግርፋት፣ስደት፣ድህነትና ወዘተ ያማረራቸዉ
የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉና፣ በስተት በኦህደድ OPDO ላይ ተስፋ አድርገዉ እንድሁም ለዉጥ ሊያመጣልን ይችላል በማለት ለOPDO
እድል ሰጥተዉት የነበሩ ሁሉ ለራሳቸዉ በራሳቸዉ ባሁኑ ጊዜ ወደ ኦነግነት ተለዉጧል፡፡ አቶ አባይ ፀሃዬ
ይሄንኑም ሲላወቀ ነዉ ወሰለኝ አንዳንድ የኦ.ሕ.ደ.ድ. ባለስልጣኖችን
ልክ ለማስገባት የዛተባቸዉ፡፡
የወያኔ
መንግስት ያሴረዉ ሴራ፣ በአዲስ አበባና በዲስ አባባ ከተሞች ልዩ ዞን ዙሪያ ብዙ ንብረት ሲላፈራ፣ የኦሮሞ ገበሬዎችን ከመሬታቸዉ
እያፈናቀለ አዲስ አባባን ከሌላ ክልል ጋር በማገናኘት፣ አዲስ አበባን ከኦሮሞ ህዝብ እጅ በማዉጣት ኦሮሞና አማራን በማጋጨት እጁን
ታጥቦ ለመብለት ተዘጋጅቷል፡፡ በተለይ ወያኔ አዲስ አበባን በደብረ
ብርሃን ከተማ በኩል ከአማራ ክልል ጋር በማገናኘት፣ከወሊሶም አሳልፈዉ ከጉራጌ ጋር በማያያዝ ኦሮሚያን በሁለት ቦታ በመክፈል አዲስ
አበባን ከኦሮሚያ እጅ ለማዉጣት የተንኮል አጀንዳ እንደለዉ ተደርሰዉበታል፡፡
የወያኔ ሴራ ቀስ በቀስ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ከተሞችን
ከኦሮሚያ ግዛት እያነጠቀ፣ ኦሮሚኛን የሚትገድልና አማርኛና ትግርኛን
የሚታወራ አዲስ አበባን ከደብረ ብርንና ከወልቂጤ ጋር
ማገናኘት ነበረ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ባለዉ አፉ፣ ወያኔ አዲስ አበባን ከአማራና ከደቡብ ክልሎች ጋር በማገናኘት
ሸገር-ፊንፊኔ የኦሮሞ አይደለችም በማለት፣ እኛ ሲንባላ ለራሱ ዘና ብለዉ ለመኖር እንደፈለግ ታዉቋል፡፡
አንድ
የኦሮሚኛ ተረት እንደምለዉ፣ “qoreen qoree hin waraantu, namni qoree lamaan
wal-waraansisuuf yaale ofumaaf waraannama” ትርጉሙም፣ ሁለት እሾኮች አይወጋጉም፣ ሁለት እሾኮችን ለማወጋጋት
የሞከረ ሰዉ ለራሱ ይወጋል ማለት ነዉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ማለት የሚፈልገዉ ነገር ቢኖር፣ በሰብዓዊ ሕሊና አማራና ኦሮሞ በወያኔ ሴራ
በመንቃት አብረዉ የወያኔ መንግስት ለመጣልና ነጻነት ለማግኝት መታገል አለባቸዉ ባይ ነኝ፡፡ ኦሮሞ ሲጨፈጨፍ አማራ አይመለከተኝም
ማለት የለበትም፡፡ አማራም ሲጨፈጨፍ ኦሮሞም ዝም ማለት የለበትም፡፡ የጋር ጠላታቸዉን በጋራ ብዋጉ የተሻሌ ይመስለኛል፡፡ ይህን
ከላደረግን በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ዉስጥም የጥያቄያችን መልስ እንደሚናየዉ ጥይት ይሆናል፡፡ እዚህ ጋር መገንዘብ
ያለበት ነገር ግን ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ስም ለአማራ የሚታገሉ፣ ለኦሮሞ ትግል ቦታ የማይሰጡም እንዳሉ መረሳት የለበትም፡፡እነዚህ
ሰዎች ለትግላችን ቦታ ባይሰጡም፣እኛ አንጎዳም፣ ድሮም ደቦ አልለመንናቸዉም፡፡ ነግር ግን ለትግላችን ጥሩ ሀሳብ ቢኖራቸዉ ለራሳቸዉ
ራሱ ጥቅም ነዉ፡፡ በነጻነታችን ቀንተዉ የሚሞቱ ሰዎች ካሉ ከወድሁ የሬሳ ሳጥን ቢያዘጋጁ መልከም ነዉ፡፡
የኦሮሞ
ህዝብ ከድሮ ጀምሮ በተደራጀና በተናጠል እየታገለ ነዉ፡፡ በተለይ በቅርብ ጊዜ የወያኔ መንግስት፣ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ
ዙሪያ ከተማዎች በተቀናጀ በጋራ ልማት ስም ያወጠዉ ማሰተር ፕላኑ
የኦሮሞን ህዝብና የኦሮሞን መሬት የሚያጠፋ ሲለሆነ በሚገርም ሁኔታ ተቋሞና ትግሉን አፏፏሜ፡፡በጣም የገረመኝ ነገር ሌላ ነግር ብኖር፣
በንጉሱ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሰሙ የነበሩ መፈክርና በቅርቡ
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሰሙት መፈክር አንድ አይነት የመሆኑ ጉዳይ
ነዉ፡፡ በንጉሱ ጊዜ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሬት ለአራሹ እያሉ ነበረ፤ በቅረቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገበሬዎች ከመሬታቸዉ
እንዳይፈናቀሉ! መሬቱ የገበሬ ነዉ እያሉ ነበር፡ለመሆኑ ወዴት እያመራን ነን?
በዚያን
ጊዜ ከተቀረጹት ፊልሞች መመልከት እንደ ቻልኩኝ፣ በንጉሱ ጊዜ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰለማዊ ሰልፍ ሲወጡ፣በዚያን ጊዜ የነበሩ
ፖሊሶች ለተማርዎች የጥይት መልስ አልመለሱም፡፡ ዛሬ ግን ወያኔ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን የጥይት መልስ እየሰጠ፣
በጠራራ ፀሃይ በ2014 በአምቦ፤በባሌ፣በጉደር፤በነቀምት፣ በሻምቡ፣በጊምብ፣በነጆ፣በአይራ፣በደምቢ
ዶሎ፣በሴላሌና ወዘተ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድል፣ በጎንደር
አከባብም 6 ሰዎችን ተኩሰዉ መግደሉ ተሰምተዋል፡፡ አንዳደም ወታደሮቹ ጦር ሜዳ መስሏቸዉ፣ በሰላማዊ ዜጎች ለይ የተኩስ እሩምታ
ሲከፍቱ፣አገሪቱ በወታደሮች ብቻ ነዉ እነደ የሚትተዳደረዉ ያስብላል፡፡ በአምቦና በባሌ ሮቤ በመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎችና
በነዋሪዎች ላይ በወያኔ የተከፈተ የተኩስ እሩምታን የሰማ ሰዉ፤ በምርጫ የወያኔ መንግስት መቀየር ዘበት እደሆነ ተገንዝቦ፣ ንብረቱን
ሽጠዉ በስደትም የዓሳ እራት ከሚሆንና ከሰዉ አገር ተዋረደዉ ከመሞት በሚሰደድበት ገንዘብ ጠበንጃን በመግዛት ከወያኔ ጋር ለመፋለም ይወስናል፡፡
ሃሳቤን
ባጭሩ ለመቋጨት፣ የኦሮሞ ሕዝብ ልማትን ጠልተዉ አይደለም የፊንፊኔ ዙሪያ የልዩ ዞን አዲስ አበባ ስር መግባትን የጠላ፡፡ የኦሮሞ
ሕዝብ ከዚህ በኋላ የወያኔን ቃል የሚያምንበት ልብ አጥቷል፡፡ እስት ሕሊና ያለዉ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ከዚህ በፊት ወያኔ በኦሮሞ
ሕዝብ ላይ የሰራዉን ተንኮል በማሰብ በኦሮሞ ቦታ ሆነዉ ይፍረድ! እኔ በበኩሌ አላምንም፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ እስር ቤቶች፣
በነርሱ ቋንቋ ማረሚያ ቤቶች 90 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የኦሮሚኛ ቋንቋ
ተናጋሪ ነዉ ይባላል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የዋሕና ለሌሎች ሕዝቦች የሚራራና ከወንጀል ጋርም የሚያስተሳስረዉ ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ
ሕዝብ ያዉቃል፡፡ የወያኔ መንግስት ግን ኦሮሞን ሲለ ፈራ ብቻ፣ ስልጣን በጨበጠዉ አጋጣሚ ተጠቅሞ፣ በኦሮሞቹ ለይ የፈጸሜ ሴራ ሲያንሰዉ፣ ጨፍጭፈዉና አስረዉ መጨረስ አቅቶታል፡፡
የኦሮሞ
ሕዝብ ልማትን አይጠላም፤እሺ እዉነትም፣ ነገሩ ለልማት ከሆነ፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞንን ከኦሮሚያ ክልል ማስተዳደር ሥር ለምን
ማዉጣት ፈለጉ? ድረዉም ሁሉም ነገር በነርሱ ትዕዛዝ እንደሚከናዉን እናዉቃለን፡፡ ኦሮሚያ ሲር ሆና መልማት አትችልም ነበር? ኦሮሚያ
ልማት ለይ አይደለችም ማለታቸዉ ነዉ? አንድ የኦሮሚኛ ተረት እንደሚለዉ፣ “bineensi bosona keessaa
gugatu/fiigu kan ciisu kaasaa” ይላል፡፡ ትርጉሙም፣ከጫካ ዉስጥ ተነስቶ የሚሮጥ አዉሬ ሌላ የተኛዉን አዉሬ ያስነሳል
ማለት ነዉ፡፡ ተረቱም እንደሚያሳየን በግድያ፣በእስራት፣በግርፊያ፣በመገልለ፣ፊትሕ በማጣት፣ በድህነት፡ በስራ አጥነት፣ ተምረዉ በመናቁና
በወዘተ የተማረሩ የኦሮሞ ተወላጆች፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ከኦሮሚያ መስተዳደር ሥር እንድወጡና አዲስ አበባ ስር ማስገባት
የተባለዉን ፒላን ለዩኒቭርሲቲ ተማርዎች በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጥይት
መልስ ሆነዉ ስለ ተመለሰላቸዉና በወያኔ መንግስት የተማረረ ሕዝብ
የተቃዉሞዉ ሰልፉን ወደ ሕዝባዊ አመጽ ቀይሮታል፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ አንዲነት ለፊትሕና ለዲሞኪራሲ ፓርቲ በ2014 በአዲስ
አበባ ባደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እዳስታወቀ፣ የወያኔ መንግስት በኦሮሞቹ ላይ እያደረገ ያለዉ ጭፍጨፋ ያሳዘናቸዉና አጥብቀዉም
እንደሚቃወሙ ገልጸዋል፡፡
የወያኔ
መንግስት ከዚህ በፊትም አማራዎችን፣ አኟኮችን፣ጉሙዞችን፣ ደቡቦችን ፣አፋሮችን፣ሶመሌዎችንና ወዘተን ሰለጨፈጨፈ ፊትሕ የሚትፈልግ
ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ ባገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ የሚትገኝ ተጨቋኝ ህዝቦች ሁሉ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ቦታ የተጀመረ የኦሮሞን አመጽ
በመደገፍ በወያኔ መንግስት ላይ ተቃዉሞዉችሁን እንዲታቀርቡ ጥሪዬን
አቀርባለሁኝ፡፡ ድል ለሰፍዉ ሕዝብ!
No comments:
Post a Comment