የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከጥቂት ጊዜ በፍት
አትዮጵያ በምግብ ራሷን መቻሏን እንድህ ብሎ ተናግሮ ነበረ፣ “በሁለት አስርተ ዓመተ ዉስጥ ሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ኩንታል በማምረት
በዓለም አቀፍ ደረጃ በምግብ ራሳችን ችለናል…” ብዙም ሳይቆይ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ለመደበቅ ብሞክርም ነገሩ የሰዉ ነብስም
ንለሆነ የምግብ እጥረትና የረሀብ ነገር በኢትዮጵያ መኖሩ የዓለም አቀፍ አጀንደ እየሆነ መጥተዋል፡፡ ፈረጆቹም ከዚህ በፊት የዉሽማቸዉ
የወያኔ መንግስት የሚለዉን እንድገት ባወደሱበት አፋቸዉ አሁን ግን የኢትዮጵያን ረሃብ እየተቀባበሉ ዘግበዋል፡፡ኢትዮጵያ ከአፍረካ ሀገራት ሁሉ
በፍትነት እያደገች ናት እየተባለች ድሮ የሚትታወቅበት የረሃብ ማለያ ለብሳ ብቅ አለች፡፡ ዛሬ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን መራብ ማለት ትልቅ ዉርደትና ዉድቀት ነዉ፡፡
15 ሚሊዮን ሕዝብ ለሌላ ሀገር ትልቅ ትረጉም አለዉ፡፡ ለምሳሌ የስውድን ሀገር አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት ሲናይ 9 ሚሊዮን ሲሆን፣
የኖርዌይ ደግሞ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ነዉ ያላቸዉ፡፡ 15 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማራብ ማለት የኖርዌይና የስውድን ህዝብ በሙሉ እንደተራቡ
ናቸዉ ማለት ነዉ፡፡
ከዛሬ ጥቂት ወራት በፊት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ እንዳሉት ኢትዮጵያ ብዙ እህል እያመረተች በምግም ራሱዋን ችላለች
ብሏል፡፡ ወገኖቻችን ሲራቡ ምግቡ ዬት ገባ? ብዙ የዉጭ ሀገር እንቨስተሮችም በእርሻ መሰማራቸዉን እናዉቃለን፡፡
መሃመድ ሁሴን ዓሊ አልሙድ ራሱ ሰፊ የእርሻ መሬት ወስዶ ሌላ ነገር ይቅርና በኢትዮጵያ የማትታወቀዉ ሩዝ ራሱ ማምረት ጀሚሮ ነበረ፡፡
እሱ ብቻ አይደለም ብዙ የትግራይ ተወላጆች በእንቨስትመንት ስም በተለያየ ክልሎች፣ በተለይ በጋንቤላና በቤንሻንጉል ጉሙዝ በእርሻ
ስራ እንደተሰማሩ የአደባባይ ምስጥር ነዉ፡፡ እና ምግቡ ዬት ገባ?
ቻናል 4.ኮም የተባለ የዉጪ ሚድያ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ መሬት ወረራና የዉጪ ሀገር ባለሀብቶች በእንቨስትመንት
ስም ብዙ መሬቶች ከገበሬዎች ተቀምተዉ ተሰጥተዋቸዉ በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተዉ እንዳሉና የተመረተዉ እህል ራሱ ወደ ዉጪ ሀገር
እንደሚላክና ነገሩ ረሃብን እንደሚያስከትል ዘግቦ ነበረ፡፡ ጆሮ የሰጠዉ ሰዉ የለም እንጂ የመሬት ወረራና የተመረተ እህል ወደ ዉጪ
የመላክ ጉዳይ አደጋን እንደሚያስከትል የዉጪ ሚዲያወች በግልጽ ዘግቧል፡፡ እዚህ በዉጭ ሀገር ከሀሻዎች ሆቴልና ሬሰቶራንት የጤፍ
እንጄራ በብዛትና በቅንጦት በብዙ ብር ሲበላ የጤፍ አምራቹ ግን እየተራበ ናቸዉ፡፡ በጎሮቤት ሀገር ኤርትራም ጤፍ ባይመረትም የኤርትራ ሕዝብ ዛሬም የጤፍ እንጄራ እየበላ
ነዉ፡፡
በደርግ ጊዜ በብዙ ኢትዮጵያ ቦታዎች በተከሰተ ረሃብ
ምክስያት ብዙ ሰዎች ሞተዋል፡፡ ፈርንጆቹም ለኢትዮጵያዉያን ለመድረስ ሲሉ ብዙ ሚሊዮን ዶላር ሲላግሱ፣ ፈረንጆቹ ለኢትዮጵያ ህዝብ የለገሱት ወደ 95
ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ግን እንዳለ ወያኔ እጅ በመግባት ለመሳሪያ ግዢና ለጥቅማቸዉ መዋሉን ቢቢሲ የቀድሞ የወያኔ ባለስልጣናት፣
አሁን ግን ከወያኔዎቹ ጋር ሳይስማሙ ቀርተዉ በዉጪ ሀገር በስደት የሚኖሩ አረጋዊ በርሄና ገ/መድህን አራያ የተባሉት ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል፡፡ http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/8535189.stm
“የወያኔዎቹ የደደቢት ቁጠባ ማህበር ያለዉ ብር፣ የኢትዮጵያ በሔራዊ
ባንክ ራሱ የለዉም…” ተብሎ
በስፋት በኢትዮጵያ ዉስጥ ሲወራ በጋዘጠኛ ጆሮ ሰምቸ ነበረ፡፡ እንደሁም ይሄንን ሁሉ ብር ከዬት ነዉ ያገኛችሁት ተብሎ ሲጠየቁ፣
ወያኔዎቹ “ከበረሃ ነዉ ያመጣነዉ” ብለዉ መልስ መስጠታቸዉን ህዝቡ ሲናገር ሰምቻለሁኝ፡፡
አቶ ገ/መድህንና አረጋዊ ያረጋገጡም ገምሱ ይሄንኑ ይመስለኛል፡፡
ዛሮም ብሆን የምዕራብያዉያንና የቻይና መንግስት የተራቡ ኢትዮጵያዉያን
ለመርዳት እየተረባረቡ ናቸዉ፡፡ የኔ ጥርጣረ ግን እንደ በፊቱ ወያኔወቹ ከዉጪ የሚመጠዉን እርዳታ ለራሳቸዉ ጥቅም ብያዉለዉስ የሚል ስጋት አድሮብኛል፡፡
ሌላ የገረመኝ ነገር ኢትዮጵያዉያን በረሃብ እያለቁ ባሉበት ባሁኑ ጊዜ የወያኔ መንግስት
የጦር ታንኮችን እያመረተ ለአፍርካ ሕብረት እየሸጠ ነዉ የሚል ዘገባ ትግራይ ኦንላይን የሚባል ድህረ-ገጽ የሲሲቲቭ ሪፖርት አያይዞ
ፅፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ የወያኔ የግል ንብረትና የወያነዎቹ ዋነኛዉ ብዝነስ መሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ጠንቅቆ ያዉቃል፡፡
http://www.tigraionline.com/articles/ethiopia-makes-tanks.html
እንደ
አንድ ሰዉ እኔ የሚለዉ፣ ማንኛችንም ከዛቺ ከኢትዮጵያ እምፓየር ዉስጥ የመጣንና በዉጪ ሀገር በስደት የሚንኖር ወገኖች ሁሉ ባገር
ቤት ለተራቡት ወገኖቻን ድምጽ በመሆን ባንድነት መቆምና መጮህ አለብን፡፡ በተበታተንን ቁጥር ወያኔ በታተኖን ይጨርሰናል፡፡ወያኔ
በጥይትና በእራት እየጨረሰ ያለ ማንን ነዉ? አሁን የተራቡት
15 ሚሊዮን ህዝብ እነ ማን ናቸዉ? ከትግራይ ክልል የራያ ህዝብ ከሌሎች ትግራይ ህዝብ ተለይቶ ለምን ተራበ…?
No comments:
Post a Comment