Thursday, January 15, 2015

የጸረ-ሕዝብ ሶፍትዌር

የመጣ በጠበንጃ፣የሚገዛ በጠበንጃ፣ራሱን የሚከላከልበት ጋሻ ግን በኮፒ ፔስት ያመጣዉን የምዕራብያዉንን ህገ-መንግሥቱ ነዉ፣ ማፍያ የወያኔ መንግስት፡፡


የወያኔ መንግስት “ጀግና ነኝ፤ በትጥቅ ትግል የሚያስበርከክኝ የለም፤ እኔ ብቻ ወንድ! እኔ ብቻ ጀግና ነኝ” ብልም ብቻዉን ከደርግ ጋር አልተፋለመም፡፡ ለነጻነታቸዉ ይዋጉ የነበሩት እንደነ የኤርትሪያ ሕዝብ ነጻነት ግንባርና የኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ነበር፡፡ በትግሉ ጊዜ፣  በደፈጣ ዉጉያ ወያኔ ኦነግን እንደ ዳዊት መዝሙሪ በማደጋግም ይዘምር ነበረ፡፡ ዛሬ ግን፣ አልቻለዉም  እንጂ የኦነግን ስም ጭራቅ ለመስመሰል ያልሳለ የስዕል አይነትና ያልፈነቀለ የድንዳይ አይነት የለም፡፡ ጊዜ የመጣለት ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንደተባለ ሁላ፣ካንድ ብርቱ ሁለት መዳንቱ እንደሚባልም፣ ሁለት ሆነዉ በኦሮሞ-ኦነግ ላይ ዳባ ፈጸሙት፡፡ ከዛሬ 20 ዓመታት በፊት ሦስቱ እናቶች የሃዘን ድንኳን  ጎሮቤት ለጎሮቤት በመትከል አብረዉ ያለቅሱ ነበረ፡፡  ዛሮ ግን ሁለቱ እናቶች ሠርግ ሲደግሱ፣ የሀዘኑ ድንኳን ከኦሮሞ እናት ደጂ አልተነቀለም፡፡ 


ማፊያዉ የወያኔ መንግስት በሻዕቢያ ጉያና በተንኮል ጉያ ስር በማሽለክሎክ ወደ ስልጣን መምጣቱ የአደባባይ ምስጥር ነዉ፡፡ ዕቢያም ሁኔታዎቹን አመቻችቶላት ከሄደ በኋላ፣ የ80 የብሄር ብሄረሰቦች ችፈራም በራሳቸዉ ቋንቋ ወደ አሸንደ ተቀየረ፡፡ የትግራይ የፖለትካ እድሮችም በእነኚ ብሄር ብሄረሰቦች ስም ተቋቋመ፡፡ የእነኚ ብሄር ብሄረሰቦች የፖለትካ እድሮች ሊቀ-መንበሩ ትግሬ ሆነ፡፡ ጻፊዉ የትግሬ ኪልስ ነዉ ሊቀ-መንበሩ ግን ትግሬ፡፡እስክርብቶአቸዉ ጠበንጃ፣ደብተራቸዉ በኮፒ ፔስት ያመጡት የምዕራብያዉን ህገ-መንግሥት፣ ቢሮአቸዉ የደደቢት በረሃና ጫካ፣ ለስብሳባቸዉ  ሕዝቡን የሚጠሩበት የስብሳባ አደራሽ ማዕከላዊ፣ቃሊት፣ዝዋይ፣ ጠወላይ፣ሀማሬሳ፣ከርቻሌ፣ መቐሌ፣ ወቐሌ፣ሲቐሌ፣ ጓዳ ጓሌ ወዘተ ወዘተረ፡፡ የሚጽፉበት ዘመናዊ ኮምፕተራቸዉ ደደቢት ሰራሽ በረኃ ወይም ጫካ ጨካኝ ጨቋኝ ጨፈጨፋ፡፡የያዙት የሶፍትዌር አይነቶች ክላሽ፣ ቦምብ፣መትርዬስ፣ፈንጅ፣ ላዉንቸር፣ታንክ፣ ወዘተ ወነበደ፡፡ የሚጠቀሙት ዊንደዉ፣ ክልል አንድን ለይተ አልማ ከክልል 9 ወይም  ተገንጥላ ያልተገነጠለች ትግራይን መልሶ ማልት ኤክፒ በሉት እምቢ፡፡  እነርሱ የሚጠቃሙበት አንት-ቫይረሳቸዉ ጥይት፣ አንት-የኢትዮጵያን ሕዝብና  አንት ሕዝብ ወርዋራ ሶፍትዌሪ፡፡ ራን እያረጉት ያለ ፐሮገራም አምባገነንነት፣ ጭቆና፣አፈና፣ግድያ፣እስራት፣ዝረፍያ፣ቅሚያ፣ አተርፍ ባይ አጉዳይ፡፡ የሚጠቀሙት የኢንተርኔት በሮዉዘር ዲሞክሬዚ ዌብሳት፡፡ በኢትዮጵያ ስም የሚጠሙበት ክይቦርድ፣ ከ60 የፍደል ጀኔራሎች 58ቱ ትግሬዎች፡፡ የሚጠቀሙበት የማዩዝ አይነት፣ ሃዳ ራይ የመለስ ራዕይ፡፡  ደኩመንት የሚይዙበት ፎልደራቸዉ ዝቅተኛ ምሁራኖችና ከፍተኛ ማሃይሞች፡፡ የሚያጫወቱት ሙዝቃ ፍርሃት፣ሲደት፣ ዲህነት፣አድሎ፣ ማግለል፣ መፈረጅ፣ መቆመር፣ መተንኮል፣ ወዘተ ወራበሳ ታተ፡፡ሁሉንም ዴታ የያዜ የእነርሱ ሲፒዩ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭንቅላት ነዉ፡፡ እኔ በጣም የገረመኝ ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሚዲያ ፕሌር ጭንቅላት፣ እያለቀሰ መዝፈኑ ነዉ! ዬት አለ ሣተናዉ ኮምፕተር ሣይንስ የተማሬ ተማሪ? የት አለ የመንተይናንሱ ሙያተኛ ራባ-ዶሪ?

No comments:

Post a Comment