Sunday, April 17, 2016

አባ ገዳ ሳይሆኑ በአባ ገዳ ስምና በሕዝብ ደም መነገድ ደምን ያፈላል፣የፈላ ደም ዋጋ ያስከፍላል!


ደም ይፈላል ይገነፍላልም። ደም  ይገላልም፣ይሞታልም። ደም ለደሙ ይደማል፤ ደም ለደሙ ይጎርፋል። ደም ይቆጣል። ደም ይቆማል። ደም ይሄዳለ።ደም ይጮሃል፣ደምመላሽን ይጠራል። ደም ከቆጣና ከገነፈለ በዙ ነገሮችን ያጠፋል፣ያጣራልምም። ወያኔ በግፍ የኦሮሞቹን ደም ሲታፈስ፣የኦሮሞቹ ደም የውሃ ጠብታ በለለበት በረሃ ውስጥ በመፍሰስ የነጻነት መስኖ በመሆን የተስፋ ጭላጭልን አስብቅለዋል። ነገር ግን በሰባአዊነትና በብልህነት ብናስብ የገናሌ፣የዳዋ፣የዋቤ ሼበሌ፣የባሮ፣የሞርሞር፣ የድዴሳ፣ወዘተ ወንዞች እያሉ በሚፈስ በሰው ደም የነጻነትን እህል መዝራት ተገቢ አይደለም።
የኦሮሞቹ ደም በወያኔ ግድያ፣እስራት፣ግርፋት፣አፈና፣ማዳላት፣ፍትህ ማሳጣትና ወዘተ መቆጣቱና መገንፈሉን በቀጠለበት ወቅት፣ ደማቸውን የከዱ የኦሮሞ ካድዎች ከወያኔዎቹ በላይ የኦሮሞቹን ደም በማስቆጣት እንድግንፍል አድርገዋል። ጅብ ሲቆስል የራሱን ቁስል ይበላል እንደሚባል ሁሉ የኦሮሞ ህዝብ በወያኔ ሲቆሲሉ፣ የኦሮሞ ህዝብ ቁስልን የሚበሉ የኦሮሞ ካደዎችም በስልጣን፣ በሀገር ሽማግለነትና በአባ ገዳነት ሽፋን የማይገባቸው የደም ጥቅም ለማግኘት ተፍ ተፍ ሲሉ አይተናል። በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩ የፊሪፋሪ ስልን ጠመኞቹ ጉዳይ ለጊዜው ወደ ጎን ተወት እናድርግና ለስብስባ ምናምን ተጠርተው የደምን ብር የቀምሱና የጣፈጣቸው፣ ባገር ሽማግለነትና አባ ገዳነት ዳባ ሲሰሩ በኦሮሞ ቄሮዎች እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
በመላዉ ኦሮሚያ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ውዲህ በመሬቱና በንብረቱ ዙሪይ ይገብኛል በማለት ተቃዉሞ በስፋት መካሄዱና አሁንም እየተካሄደ እያለ እንደሚታወቅ ሁሉ፣ በኦሮሚያ ክልል ብጉጂ ዞን ውስጥም ተካህደዉ የንጹሃኑ ደም ፈስሶበታል። ሼክ መሃመድ ኣላሙዲን ከጉጂ ዞን ከሻኪሶና ከሳካሮ ለ17 ኣመታት በላይ ቀንና ሌሊት፣ ቅዳሜና እሁድ፣ እንድሁም የበኣላት ቀንም ሳይቀር በየኣመቱ  4.5 ቶን ወይም 45 ኩንታል ወርቅ እያመረተ ይግኛል። ይህ መረጃ ከእነርሱ ድርጅት ዌብሳይት ላይ የተገኘ ሲለሆን፣ እውነተኛው ምርት ከዚህ በላይ ልሆን ይችላል። ሼክ መሃመድ ኣላሙዲንና ወያኔዎቹ የከበሩበት አንደኛው ምንጭ ከጉጂ በዘረፉት ወርቅ ነው። ሼክ መሃመድ ኣላሙዲንና ወያኔዎቹ ከለጋደንቢና ከሳካሮ ለ17 ኣመታት የዘረፉት ሳይብቃቸዉ አሁንም ዳዋ ኦኮቴ የሚባል  ድንግል ቦታ ወስዶ ለመበዝበዝ ሲዘጋጅ ከህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞና ቁጣን አስነስተዋል። በሚገርሚና በሚያሳዝን ሁኔታ አባ ገዳም ሳይሆኑ ራሳቸዉን አባ ገዳ ያደረጉት አቶ ቦኮ ጋናሌ የሚባለውና ግብር አበሮቻቸው የጉጂ ህዝብ የማያውቀውን ‘የጉጂ ኦሮሞ የአባ ገዳዎች ማህበር’ የሚባልዉን በፊንፊኔ ዉስጥ እንዳቋቋሙት  ተደርሰውበታል። ይህ በዚህ እንዳለ በስርአቱ የተመርጡና በመላው ሀገርና በሚዲያ የታውጀለት  የጉጂ አባ ገዳ፣ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ  እያለ እነኚ ከደም ገባታ መብላት የለመዱ አባ ገዳ ባዮችና ጃሌዎቹ በጉጂ አባ ገዳነት ስም ማህተም በማስቀረጽ አምስት ሚሊዮን ብር መጠያቃቸዉን፣ እነርሱ ራሳቸው በ 15,07,2008 ወደ ምድሮክ ውርቅ ኩባንያ ከጻፉት ደብዳቤ መረዳት ተችለዋል። እነኚ የደም ነጋዴዎች ከህዝብ የወጡና ከዝብ ማምለጥ እንደማይችሉ አውቀዉ የሚበላቸዉን የደም ገንዘብ ከመብላት እንድቆጠቡና ወደ ህዝባቸዉ እንድመልሱ በጣም ጠባብ በር ብቻ እንደቀራቸው ተስተውሏል።        

                              

           No comments:

Post a Comment