Tuesday, April 26, 2016

ወያኔ የኦሮሞን ሕዝብና ሌሎች ኢትዮጰዉያኖችን ለመግደል ጥይት ሳያንሰው መድሃንትን በአደባባይ መጀመሩ ታወቀ


ልበሏት ያሰቡትን ዶሮ ዥግራ ናት ይሏታል እንደሚባለው ሁሉ፣ የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ምሁርና በሀገር ውስጥ የሰላምን ትግል ዋናዉ አማራጪአቸው ያደረጉት የተቆዋሚ የፖሊቲካ መሪዎችና አባላትን የኦነግን ታፔላ ለጥፈውላቸዉ እያንከራተቱዋቸዉ ይገኛሉ። ለህዝብና ለሀገሩ ተቆርቋሪ የሆነዉን ሰዉ፣ ኦሮሞ ከሆነ ኦነግ፣ አማራ ከሆነ ግንቦት 7 ወይም ቅንጂት እያሉ ወያኔና ጃሌዎቹ እራሳቸው አሸባሪ ሆነው በአሸባሪዉ ታፔላ ሀገርን ያሸብራሉ። አብሮ እንዳልታግሉ ሰዉ፣ የኦነግን ስም ጭራቅ በማስመስል ሰዎቹን ለማታለል አየሞከረ ያለዉ የወያኔ መንግስት፣ ብልጥ ብሆን ኖረዉ ህዝቡ ለኦነግ ያለዉ ፍቅር አይቶ መገረምና በመፍራት ደባ መሸረብ ብቻ ሳይሆን ለሀገሩ ዘላቂ ሰላም ሲባል ህዝቡና ኦነግን ማገናኘት ወይም መቶ በመቶ የህዝብን ጥያቄ መመለስ ነበረ። የሰላም ብልጭታ ያላቸው መንገዶች ሁሉ በመዝጋት በዜጎቻችን አእምሮ ውስጥ፣ ወያኔ የሚያዉቀው በጦርነት መንገድ ብቻ  ሰዉ እንድመራ እየጋበዘ ነዉ።
                   
ፎቶ ከኦላይን      
ወያኔ ምኑን ይዞ ምኑን መልቀቅ እንዳቃተዉ የሚያሳየን ብዙ ፍንጮች አሉ። መጀመሪያ ላይ የኦሮሞ ተማሪዎች የወያኔን የመሬት ዘረፋንና ግፍ በሰላማዊ መንገድ ሲቃወሙ፣ “ይህ የጥቂቶቹና የዱሪዬዎች ጥያቄ ነዉ፣ምዛን የሚያነሳ አይድለም” አለ። ቀጥሎ፣ “ ጥያቄ የሚያነሱ አንዳንድ የጠላትን አጀንዳ የሚያራምዱ ናቸዉ፣ የኦነግና የግንቦት 7 እጅ አለበት” አለ። አሁንም ቀጥሎ “ህይንን የኦሮሞ ህዝብ የጠራና ያነሳሳብኝ ጋኔንና ጦንቃይ ነው” አለ። በመቀጠል ደግሞ፣ “የሕዝብ ጥያቄ ልክ ነው ችግሩ የመንግስት ነዉ፣ መንግስት ለተጠረው ስህተት ይቅርታ ይጠይቃል፣ ላለፍዉ ለሰው ነብስም ካሳ ይከፍላል” አሉ።  ይህ በእንድ እንዳል ሰሞኑ ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚንሰማ ነገር ለጆሮ እንኳን የሚሰቀጥጥ ነው። ይቅርታ የጠየቀችው ወያኔ ተመልሳ በኦሮሞ ፌደራልስት ኮንግረንስ ፓርቲ አመራሮች ላይ መንገድ ቅይሳ ክስ ከፈተች። ውሃ የወሰደ ሰው አረፋን ይይዛል እንደሚባለው፣ ወያኔ ከገባችበት ከህዝብ ቁጣ ባህር ውስጥ ለመውጣት አረፋን በመያዝ፣ “ህዝብን ለአመጽ አነሳስታቸኋል፣ከኣኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ተግናኝታችኋል፣ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የኦነግ ልሳን ነው፣ ጃዋር ሞሃመድ የኦነግ መሪ ነዉ፣” ወዘተ በማለትና በመቀባጠር የከሰሱት ሳያንሳቸዉ፣  በቁጥጥራቸው ስር ያሉት የኦሮሞ ፌደራልስት ኮንግረንስ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት እነ አቶ በቀሌ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ ጉርሜሳ  አያኖ የማያቁት መድሃንት እንድውጡ መታዘዛቸው ደምን ያፈላል! ይህ የሚያሳየው፣ ወያኔ የኦሮሞን ሕዝብና ሌሎች ኢትዮጰዉያኖችን ለመግደል ጥይት ሳያንሰው መድሃንትን በአደባባይ መጀመሩ የሚያሳይ ፍንጭ ነው።  
ወያኔ ግን አተርፍ ባይ አጉዳይ እየሆነ እያለ የሚነግር ሰው ጠፍ እንደ? ጆሮ ዳባ ልበስ እያሉ በሰዉ ደም እጃቸዉን ታጥቦ በኋላ ላይ እነርሱን ራሳቸው ተመልሶ የሚበሉዋቸውን መብላት ምን ዋጋ አለዉ? ትርፉ ግን  የዘሩትን ቂም በቀል በቅርቡ ያጭዳሉ! አዝመራዉም ደርሰዋል።  በዳንኤል ባሪሶ አሬሪ  (መያዚያ 18, 2008 ወይም አፕሪል 26, 2016)።       

No comments:

Post a Comment