Saturday, November 12, 2016

2ኛ መልስ ለጉጃ ወይም ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦና ለመሰሎቻቸው

Hi Guja,
ለአስተያየተ መልስ ስለሰጠኽኝ አመሰግናለሁ፣ ነገር ግን መንነቱን ደበቆ መልስ የሚሰጥ ወይም የሚናገር ሰው አላበረታታም እኔ። ሆኖም ግን ትንሽ ሃሳብ ለመስጠት እፈልጋለሁኝ። እንተ ስጀመር ለምን እራስህን ደበቀ መጣህ? ይህ ፌስ ቡክ የካዎ ጦና አይደልም። እንደዚህ የሚደበቁ ሰዎች በብዛት ሰላዮችና በራሳቸው የማይተማመኑ ሌላም ግልጽ ያልሆነ አጀንዳም ያላቸው ናቸው።

 የካዎ ፎቶ የፕሮፋይል ፎቶ መድረግ ትችላለህ ሆኖም ግን ዶ/ር ኋይሌ ላሬቦ ስም ቀይሮ መጥቶ  እርሶ ብዬ መጥራት ስገባኝ አንተ እዳልለው ሰግቸ ነው። ዶክተር ይቅርታ፣ ዶክተር አልኩህ እንዴ፣ ዶክተሩ ስም ቀይሮ መጥቶ ይሆናል የሚል ንፋስ ሽዊ ስላለብኝ ነው። “/ ባሉት ላይ በተለይም የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር እኔንም ግር አሰኝቶኛል” ብለሃል። የኦሮሞ ህዝብ ብዛት ብቻ ለምን ግራ ይገባሃል? ለምን የናይጄሪያ  ውስጥ የሚገኝ በቁጥር ብዙ የሆነ የሃዉሳ ህዝብ አላሳሰበህ? እነርሱ የውጭ ናቸው ስለ ሀገራችን ነገር ነው የሚናወጋ ካልክ፣ ከኦሮሞ ቀጥሎ ያለው ስለ አማራ ህዝብ ቁጥር ለምን አላሳሰበህ? ኦሮሞ ለምን በዛክ ወይም ሌሎቹ ለምን ተደባለቁበት ነው የሚትለኝ? እንደዛም ከሆነ አማራ ቅልቅል የለውም?  የዓለማችን ሀግሮች የዘመናዊ ዜግነት ሳይሰጡ በፊት እኮ ኦሮሞ በገዳ ስርዓት በሞጋሳና በጉድፋች ዘግነት ይሰጥ ነበር እኮ! ሌሎቹ “እኛ በእግዚአብሔር የተመረጥን ምርጦች ነን” ሲሉ፣ ኦሮሞ በሞጋሳና በጉድፋቻ ያመጣውን ሰው ስጋት እንዳይንሰማ የበኩር ልጅ በማድረግ ብዙ ከብቶችና ንብረት ይሰጠዋል። ይሄ እኮ እንደ ስልጣነ መታየት አለበት ጎበዝ! ተው እወነቱን አውሩ! ኦሮሞቹ ብዙ ሆኖ ሳሉ እኛ ለምን አናሳ ሆነን ከልክ እሱ ዬትም ሀገር ያለ ነገርና ዕድል ነው። በኦሮሞ ዘንድ እንኳን ሰው እንስሳ፣ እንጨትና መሬት ክብርና መብት አላቸው፣ በኦሮሞ አብዮት ስጋት እንዳይገባህ ወንድም!

እውነትን ለመደበቅ አትኮምክ፣ እዉነት ብትኮመክም ሁል ጊዜ እዉነት ነች! “ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔር ጭቆና አልነበረም ብሄራዊ  ጭቆና እንጅ” ለምለው የዶክተር ኋይሌን ሃሳብ ትጋራለክ ወይም አሁኑኑ ለዚህ ሃሳብ ሽንጥህን ገትረህ ትከራከራለህ። አንተ ያቀረበከውን ምሳሌ መልሸ ላንሳና ልተነትን፣ “አይቼበታለሁ....ለምሳሌ በብዛት የኦሮሞ እና አንዳንድ የደቡብ ፖለቲከኞች ባሪያ ሆነው ይሸጡ እንደነበር በመጥቀስ የብሄር መብት ጥሰት እንደነበር ብለው ሲያራምዱ እንደነበር ይታወቃል። ድርጊቱ እውነት ሆኖ ሳለ...አፈጻጸሙ ግን በብሄር ላይ የተመሰረተ በፍጹም አልነበረም.....ምክንያቱም በአሁኑ ግዜም ቢሆን ቢያንስ እኔ በማውቀው አንዳንድ ደቡብ ክልል....ህብረተሰቡ እራሱ እራሱን በተለያየ ደረጃ ነው የሚያየው....ግማሹ የተከበረ ሲሆን የሚናቁም በዛው ደረጃ አለ ራሱንም እያስተዳደረ ባለበት ሁኔታ.....በድሮም ጊዜ ቢሆን የየብሄሩ መሪዎች የራሳቸውን ብሄር ይሸጡ እንደነበር አይካድም”- ስላልክውና እንደ ምሳሌ ያሰሳኽው ደቡብ ውስጥ እውነትም ህዝቦች እራሳቸው ሆነው እራሳቸውን እያስተዳደሩ ነው ያሉት ዛሬም ብሆን? አንተ እንዳልክው ደቡብ ውስጥ እስክ ዛሮም ግማሹ ተክብሮ እያሉ ግማሹ ለምን ተናቁ፣ ምስጥሩን ታውቃለህ? ታድያ ነገር የብሄር ጭቆና ካልሆነና ብሄራዊ ጭቆና ክሆነ በንተ ፎርሙላ ራሱ ሌላ ብሆር ስከበር ሌላ ልምን ተናቀ? ተው እውነት ብናወራ ይሻለናል። “qaroon qaroo sobe galata hin qabu” ይላል አንድ የኦሮምኛ ተረት-ትጉሙም ‘ብልህን የዋሸው ብልህ ሰው ምስጋና አይኖረውም’ ማለት ነው። ከፊዳሎችና ከነፍጠኞች የኢትዮጵያ ህዝብ የወረሰው ነገር የለም እንዴ? እስከ ዛሬ ድረስ ምኒልክ ዘመናዊ ኢትዮጵያን ከፈጠረ ጊዜ ጀሚሮ ብሄር ብሄረሰቦች ባራሳቸው ቁጥር የተፋፍላቸውን የስልጣን ጫማ አድርገው እራሳቸውን አስተዳድሮ አያውቁም፣ ለሌላ ሰው የተሰፋ ጫማ ወይ የሚጠባቸውን ወይም የሚሰፋቸውን፣ ወይም በግማት ሌሎቹን የሚያስሸብሩበትን ጫማ እንድያደርጉ ተደርገው ነው እያስተደድሩ የነበሩና አሁንም እያስተዳደሩ እያሉት።

አንተም እንዳልከው በብዛት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተካዮች አማራና ትግሬ ናቸው ብለሃል። እምነት ብሄር የለውም ለልከው ልክ ነህ፣ ነገር ግን የኦርቶዶክስ እምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የግላቸው አደርገው ይሚያስቡና የኦርቶዶክስ እምነት  ለሌሎች ብሄሮች እንደማይገባ እድርገው የሚያስቡ ሰዎች ዛሬም አሉ ትናንትም ነበሩ። ለምሳሌ ራዕይ ማሪያም በሚለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት መጽሃፍ ገጽ 37 ላይ “ጋላ፣ ፋላሻ፣ሻንቅላ” እንጉማን እንደ ሁኑና ማሪያም እንደማትወዳቸው ደብተራው ጽፎዋል።

 በዛ በተበላሸ  አመለካከት የሚያምኑ ዛሬም ቢሆን ብዙ አሉ። በድሮ ጊዜ ኦሮተዶክ ማለት የንጉሶች ግራ እጅ ነበረች። ዘሬም ብሆን በኢትዮጵያ በ 100ና በ50 የብር ኖት ላይ ለዚህ ነው ያኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ጳጳሶች በአስትራክት መልክ የሚናገኘው። እኔ ክስቲያንም ቢሆንም ኢትዮጵያ እንደሚትባለው ‘የክርስቲያ፣ የነጠላ፣ የአማሪኛ፣ የእስክስታና’ የወዘት ሀገር ብቻ እይደለችም! ይሄንን የተበላሸ ታሪክ በእዉነታ ላይ ተመስርተን ካልሰራንበትና ካልስተካከለው ወይም የአደባባይ ምስጥር የሆነውን ነገር ለመደብቅ የምንፈልግ ከሆነ ለሁላችንም የሚትሆንና የሚንመኛት ኢትዮያን አናገኛትም። ቼር ሰንብት!



 ከዳንኤል በሪሶ አሬሪ

No comments:

Post a Comment